Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.66K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-04-17 12:41:18 በትንሳኤ በዓል  ዋዜማ ሁለት የእጅ ቦንቦችን ይዞ የተገኘው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዋለ

በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን የአርባምንጭ ከተማ  የፖሊስ አባሉ በትንሳኤ በዓል  ዋዜማ ሁለት የእጅ ቦንቦችን ይዞ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆነዉና የቀድሞ መከላከያ ሰራዊት አባል የነበረው ይህ ግለሰብ ባለቤቱን እገድልሻለሁ እያለ በእጅ ቦንብ በተደጋጋሚ እንደሚያስፈራራት ከአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ የእጅ ቦንቡ ሊገኝ ችሏል ።

ፖሉስም ቦንቡን የያዘውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በተጨማሪም በትንሳዔ በአል ዋዜማ ምሽት ሲንቀሳቀስ ፖሊሶች በጥርጣሬ አስቁመዉ በፈተሹት አንድ ግለሰብ እጅ አንድ የእጅ ቦንብ ተይዟል ።

ተጠርጣሪዉ የመከላከያ ሰራዊት አባል መሆኑና ለእረፍት ወደ አርባምንጭ ከተማ መምጣቱ በተደረገው ምርመራ ቢረጋገጥም እረፍት የሚወጣ የመከላከያ ባልደረባ ትጥቅ መያዝ ስለማይችል ከሚሰራበት ክፍል ጋር በመነጋገር የእጅ ቦንቡ ተቀምቶ ግለሰቡ በዋስ መለቀቁን ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ዳጉ ጆርናል
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.0K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 12:01:05 በታላቅ ቅናሺ ምንምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ

የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች

➠ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
➠ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
➠ የ ድርጅት ማስታወቂያ
➠ የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
➠ የ ቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ
➠ ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች ማስታወቂያ

የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
➲ እንዲሁም የተለያዩ የ Business ስራወችን ከእኛ ጋ መስራት ለምትፈልጉ አናግሩን

ምርትና አገልግሎቶን በተመጣጣኝ ዋጋ ለቻናላችን ቤተሰቦች ተደራሽ በማድረግ በእጥፍ ያትርፉ።

አሁኑኑ ያናግሩን

ለማናገር
• @Dani_peromotor
397 views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 11:56:06 Inbox #ራያ
አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ራያን ሊረከብ አርሚ 44ኛ እሚባለውን ጦሩን አስጠግቷል፣ህወሀት ከኮረም እስከ ዋጃ ያለውን የራያ ከተሞች እሚያስተዳድሩለትን የዞን፣የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮችን ከወዲሁ አዘጋጅቷል።
አማራ ክልል ያስቀመጣቸው የፀጥታ አካላት እና አለማጣን ጨምሮ በተለያዩ የራያ ቀበሌዎች የተመደቡ የሲቪል አመራሮች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መተላለፉ ተሰምቷል።
ሚያዝያ 9/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.2K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 11:55:58
በርካታ ታንኮች ወደ ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እያመሩ ይገኛሉ። ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው።
Chaos continues in Sudan capital,Khartoum.
ሚያዝያ 9/2015 ዓ.ም
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.2K views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 11:55:58 በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ
በአገሪቱ ጦርና በፈጥኖ ደራሽ ሐይል መካከል በሱዳን መዲና ካርቱም የተነሳው ግጭት በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ችግር ላይ እንደጣላቸው በስፍራው የሚገኙ አንድ ኢትዮጵያዊ ለኢትዮ ኢንሳይደር ተናገረዋል፡፡ ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ኢትዮጵያዊያኑ በአሁኑ ስዓት በግለሰቦች ቤት ተጠልለው እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

በአቡድልፋታህ አልቡርሃን የሚመራው የሰዱን ጦር እና በሀምዳን ዳጋሎ በሚዘወረው የፈጥኖ ደራሽ ሐይል መካከል የተቀሰቀሰው ‹ የከተማ ግጭት › ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ቢያንስ የ100ሰዎችን ሕይወትን መቅጠፉ ተዘግቧል፡፡

በካርቱም የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያኑ ሁለቱ ሀይላት እየተዋጉ ያሉት ከተማ ውስጥ በመሆኑ ‹ ነገሩን ከባድ › አድርጎታል ባይ ናቸው፡፡ እኚሁ ኢትዮጵያዊ የሚመለከታቸው ሲሉ የጠሯቸው አካላት ከካርቱም መውጣት የሚችሉበትን መንገድ እንዲያመቻቹላቸው ጠይቀዋል፡፡

በካርቱም የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ኤምባሲው ‹ ከግጭቱ ጋረ በተያያዘ ሊያጋጥም ከሚችል አደጋ ራስን መጠበቅ አስፈላጊ › መሆኑን አስታውሶ ‹ ኢትዮጵያዊያን ከግጭት አካባቢዎች በመራቅ፣ ከእንቅስቃሴ በመቆጠብ ራሳቸውን ከአደጋ እንዲጠብቁ› አሳስቧል፡፡
ኢትዮ ኢንሳይደር
ሚያዝያ 9/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
1.2K views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 11:55:58
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ከዓለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ ሃላፊዎች ጋር ሲያደርገው የቆየው ውይይት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘባ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ሃላፊዎች ጋር ለአንድ ሳምንት ሲያደርገው የቆየው ውይይት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እና በብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተመራው ልዑክ ከዓለም ባንክ እና ከዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዳይሬክተሮች ጋር ሲያደርግ የነበረው ውይይት መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ለአንድ ሳምንት በቆየው ውይይት፤ የፋይናንስ ልዑኩ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ እና ልዑካቸው ጋር ምክክር ማድረጉን አንስተዋል፡፡
በኹለቱ አካላት መካከል የተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የልማትና ሰብዓዊ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል መሆኑንም አምባሳደር ስለሺ ጠቁመዋል፡፡
ሚያዝያ 9/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
1.2K views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 11:51:25 በሱዳን በተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት እስካሁን ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸውን CNN ዘግቧል።
1.3K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 21:50:07
የፈጥኖ ደራሹን ሀይል የሚደግፉት አገራት የሚከተሉት ናቸው ሲል የሱዳኑ ዋሃድ ጋዜጣ አስነብቧል።
አዲስ አበባ፣አስመራ፣ሞስኮ
ዱባይ እና ቻይና ናቸው ብሏል።
እነዚህ አገራት የፈጥኖ ልዮ ኮማንዶውን ጥቃት ሲያቀነባብሩ ነበር ሲል ነው የሱዳን ዋህድ ጋዜጣ የዘገበው። በዚህ አክሎም 11ሺ ጦር ኤርትራ ውስጥ ሲሰለጥኑ እንደኖሩና አሰልጣኙ ሻዕቢያ መሆኑንም ነው ጋዜጣው የዘገበው። ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ የልዮ ፈጥኖ ደራሹ አዛዥ መሀመድ ሀምዳን ጋደሎ ( አህሜቲ) ከአዲስ አበባ መንግስት ጋር 4 ጊዜ የስልክ ልውውጥ አድርጓል ነው የተባለው። የአገሪቱን ጦር የመገናኛ ሬዲዮ የጠለፉት የሩሲያ መንታፊዎች ሲሆኑ ሞሳድ ለማስለቀቅ ቢጥርም እስካሁን አልተሳካለትም ብሏል ጋዜጣው።ሱሌማን አብደላ
ሚያዝያ 8/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.0K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 21:13:55 የሱዳን ዋና የቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ ስርጭት አቁሟል።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.0K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 20:50:00
በሂሚቲ የሚመራው እራሱን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ብሎ የሚጠራው ጦር ላይ ዛሬ በፖርት ሱዳን በሌላ ሀገር አየር ሃይል መመታቱን ገልጿል። ምናልባት ግብጽ ሳኮን አትቀርም የሚል መላምቶች እየተሰጡ ነው። ትናንት በነበረው ውጊያ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር በርካታ የግብፅ ወታደሮችን ማርኪያለሁ ማለቱ ይታወሳል። ለዚህ የአፀፋ ምላሽ ይሆን?።
ሚያዝያ 8/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.1K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ