Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 220

2022-08-28 22:17:28
ወያኔ ከፉከራ ወደ ልመና
ወያኔ ጭንቅ ላይ ናት

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.1K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:43:07
ሰበር ዜና

በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመራው ጥምር ጦር ዋጃ ከተማን በቁጥጥሩ ስር አውሎ ወደ አላማጣ እየገሰገሰ ነው የትግራይ ወገናችን ሊነጋለት ነው።

በሌላ በኩል

ሽራሮ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ገብታለች

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.4K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:42:35
ክብር ለመከላከያ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.4K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:42:05
1.3K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:09:58 ዋጃ
ዋጃ አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ ይሰማል!!! አብዛሀኛው ቆቦ አካባቢ ያለው ወራሪ ወደ ትግራይ አቅጣጫ እየተመለስ ተራራዎች ላይ እየሰፈረ ነው!!! ጀግኖቹ አራዱም የነበረውን ወራሪ እረፍርፎታል!!!
የቻናሌ ቤተሰብ ይሁኑ፣ለሌሎች ጋብዙ በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ https://t.me/+zsQENK1iuHYzMDFk
1.6K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:06:45
"...የትግራይን ጨቅላ ህፃናት ከከንቱ እልቂት የመታደግ ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታ አለብን ነው ያልነው" :- የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገራዊና ህዝባዊ ኃላፊነቱን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየፈፀመ መሆኑን ገለጸ!!


መከላከያ ሠራዊት ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው አሸባሪው ህወሓት የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱ፣ እኔ እየመራሁ የማልዘርፋት ሀገር ትፍረስ እኩይ ተግባሩና ፀረ ህዝብ ባህሪው አንፃር የሚጠበቅ ነው። በተቃራኒው እኛ ግን የመላው 120 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵውያን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ተቀብለን የምንፈፅም ህዝባዊና ፕሮፌሽናል ብሔራዊ ኃይል ስለሆንን መላውን ህዝባችንና የትግራይን ጨቅላ ህፃናት ከከንቱ እልቂት የመታደግ ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታ አለብን ነው ያለው፡፡

ስለሆነም መከላከያ ሰራዊት ህግን ተከትሎ ወገኑን ከሰቆቃና እልቂት ለመታደግ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት በጀግንነት በመክፈል የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም ያስከብራል ነው ያለው፡፡

ስለሆነም መከላከያ ሰራዊት ህዝባችንን ከዚህ አሬመኔ ቡድን ቀንበር ለማላቀቅና ከከንቱ ጭፍጨፋ ለማዳን ህዝባችንና ለሀገራችን ይጠቅማል የተባለውን ሁሉ በመስዋዕትነታችን እውን ለማድረግ በከፍተኛ ብቃትና የላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

እኛ ታላቅና ታሪካዊ ኃላፊነት ካለበት የመከላከያ ኃይል በሚጠበቅ አግባብ፣ ሁለተናዊ በሆነና ነገን አሻግሮ በሚመለከት እሳቤ እንዲሁም በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የምናደርገው እና እናንተ በጋለ ጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት ዛሬ፣ አሁን፣ እዚችው እዲሆን የምትፈልጉትን ሁሉ "አፍ በእጅ በሚያስይዝ" አስተማማኝና ዘላቂ በሆነ ድል ይታረቃል ሲልም አረጋግጧል፡፡
 
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.5K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:06:16
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አልጀርስ ገቡ!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አልጀርስ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአልጀሪያ ርዐሰ መዲና አልጀርስ ሲደርሱ የአልጀሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር አይመን ቤን አብድራህማኔ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቆይታቸው ከአልጀሪያ ፕሬዚዳንት አብድልመጅድ ተቡኔ ጋር የሚወያዩ ሲሆን የተለያዩ የልማት ስፍራዎችንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
  @ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.4K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:35:51 መግለጫ

ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን በተመለከተ ከሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ!!

ከኢትዮጵያ አልፎ በአጠቃላይ ለአፍሪካ ቀንድ አገሮች ሰላምና መረጋጋት ጠንቅ የሆነው አሸባሪው የህውሓት ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ በአማራ ክልልና በአፋር ክልሎች ላይ የከፈተውን ደም አፋሳሽ ጦርነት የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት በፅኑ ያወግዛል።

አሸባሪው የህውሓት ቡድን ለ27 ዓመታት የአገሪቱን ማእከላዊ ስልጣን ተቆጣጥሮ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ኢሰብአዊ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተጨማሪ በአገሪቱ ህዝቦች መካከል እርስ በርስ መተማመን እና መተባበር እንዳይኖር የሚያደርግ ጥላቻ በመንዛት የከፋ ስቃይና መከራ ያደረሰ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

ቡድኑ የአገሪቱ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ በነበረበት ዘመን የሶማሌ ክልል ህዝብን ገድሏል፤ አፈናቅሏል ፣ ሴቶችን ደፍሯል፣ ተቆጥረው የማያልቁና ለማመን የሚከብዱ ዘግናኝ የጭካኔ ተግባራትን ሁሉ አንድም ሳያስቀር ፈፅሟል፡፡

ከዚህም አልፎ ለርካሽ ፖለቲካና ለስልጣኑ ቀጣይነት ሲል ሴራ በመጎንጎን የሶማሌ ህዝብ  ለዘመናት አብረው ከኖሩት ኢትዮጵያዊ ወንድም እህቶቹ ጋር እንዲጋደልና ደም እንዲቃባ አድርጓል የክልሉን ሃብት በመዝረፍ እና የጥቂት ሰዎች ኪስ ማደለቢያ በማድረግም ክልሉ በልማት ወደ ኋላ እንዲቀር አድርጓል፡፡

ይሔ አሸባሪ ሀይል ባለፈው ግፍና በደሉ ከመፀፀት ይልቅ አሁንም የሶማሌ ክልልን በማተራመስ ህዝቡ ያገኘውን ሰላምና ነፃነት ለመንጠቅ በአንድ በኩል በክልሉ አዋሳኝ ከሚገኙ ወንድም ሕዝቦች ጋር ሰላም እንዳይኖረው ግጭት በመጥመቅ፣ በሌላ በኩል ከአልሸባብ ጋር ያልተቀደሰ የጥፋት አጋርነት በመፍጠር ክልሉን የማተራመስ እና አገር የማፍረስ ቅዠቱን ለማሳካት እየተራወጠ ይገኛል።

አሸባሪው ህውሓት ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እየተጋለበ በከፈተው ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚኖሩ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል፤ በእድሜ ልክ ድካም የተከማቸ የሚሊዮኖችን ሀብትና ንብረትም በከንቱ አውድሟል።

የዚህ ባንዳ ቡድን ዋነኛ ሀሳብ ኢትዮጵያን እኔ ወይም የኔ ተላላኪ የሆነ ሀይል ካልመራት አፈርሳታለሁ የሚል ሲሆን ይህን በጤነኛ አእምሮ ሊታሰብ የማይችል ከክፋት ሁሉ የከፋ ሀሳቡን ለማስፈፀምም ለሶስተኛ ጊዜ ጦርነት በመክፈት ምስኪን የደሀ ልጆችን በአደንዛዥ እፅ እያደነዘዘ ወደ እሳት እየማገደ ይገኛል።

ቡድኑ የያዘው እኩይ አላማ ለአገራችን ሁለንተናዊ ሰላም እና ልማት ፀር መሆኑን የሚገነዘበው የሶማሌ ክልላዊ መንግስት እና ህዝብ በምስራቅ በኩል የህወሃት አጋሮች በሆኑት እንደ አልሸባብ ባሉ የሽብር ቡድኖች የሚሞከሩ ሙከራዎችን በማክሸፍ እና በመደምሰስ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ከማስከበር ባሻገር  በህወሃት ላይ በሚወሰደው እርምጃ እንደሁልጊዜው ያልተቆጠበ ድጋፉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በአፅንኦት እየገለፀ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑንም ያረጋግጣል፡፡

በመጨረሻም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ቡድኑ የጀመረውን ጦርነት አቁሞ በኢትዮጵያ መንግስት የቀረበውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበል ተገቢውን ጫና እንዲያሳድር የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።

የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ  መንግስት
ነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም
ጅግጅጋ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.6K views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:29:00 ሮቢት ላይ ተቆርጠው የነበሩት ሁሉም እጁን ሰጥቷል። ቆቦ ዙሪያዋን ጥምር ጦሩ ከቧል። ቆቦ ውስጥ ያለው ወደ አላማጣ ፈርጥጧል። ኮማንዶ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.6K viewsedited  17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:27:57 የኤርትራ ሠራዊት ወደ ሁመራ አቅራቢያ ተከዜ ከፍተኛ ሀይሉን አስፍሮዋል። አየር ሀይሉ ከፍተኛ ቅኝት እያደረገ ነዉ ትላንት በዛላንበሳ የተጠጋዉን የወያኔ ጦር አየር ሀይሉ እንዲበተን አድርጎታል በባድመ በሽራሮ ዛላንበሳ ትንኮሳ አለ።
የቻናሌ ቤተሰብ ይሁኑ፣ለሌሎች ጋብዙ በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ https://t.me/+zsQENK1iuHYzMDFk
1.6K viewsedited  17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ