Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.66K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 212

2022-09-04 18:19:32 አሁናዊ መረጃ
ሰቆጣ ግንባር
ሰቆጣ ከተማ ሰላም ነው።
በሰቆጣ በወለህ ውቅር እሚባል ቦታ ላይ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህ ግንባር የተሰለፉ የህወሓት ታጣቂዎች ብዛት በጣም ብዙ እንደሆነ ታውቋል።
የህዝቡ ደጀንነት በቃላት የሚገለፅ አይደለም፣ቡና ሳይቀር ለሰራዊቱ ግንባር ድረስ በመውሰድ እያበረታቱ ይገኛሉ።
ራያ ግንባር
በግዳን በኩል በተኩለሽ፣በቀይአፈር እና በድኖ አሁን ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው።
በአላውሃ ማዶ በባቡር መንገዱ እና በአስፋልቱ መካከል ካለው ሜዳ ላይ እና ተራራ ላይ ከፍተኛ ውጊያ አለ።
በወርቄ በኩል አሁንም ድረስ የሞት የሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል።
በራያ ግንባር የህወሓት ታጣቂዎች ማጥቃት ላይ ሳይሆን መከላከል ላይ ያተኮረ ስራ ነው በአብዛኛው እየሰሩ ያሉት። ሙሉ ማጥቃት ደግሞ በሰቆጣ በኩል አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነው።
ሁኔታው በየሰዓቱ ስለሚለዋወጥ ያለውን ነገር ለማድረስ በቻልኩት እጥራለሁ።

https://t.me/+zsQENK1iuHYzMDFk
3.0K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 17:00:55 #ሰበር ዜና የቴሌግራም ቻናላችን ለናንተ ለቤተሰቦቻችን በቴሌግራም መረጃዎችን ካሉበት እያነፈነፍን እያደረስን መሆኑ ይታወቃል
አሁን ደግሞ #በYouTube መጥተናል እየገባችሁ እንድታበረታቱን በትህትና እንጠይቃለን

https://youtube.com/channel/UCw9EUpuNrwP0hLvdmXz-ZBQ
3.4K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 14:00:33
ሰበር ዜና-|አስደሳች ዜና ከግንባር-|ሌሎችም አሁናዊ ጥብቅ መረጃዎች
መሉ መረጃዉን ይመልከቱ



3.8K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 13:26:40
ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ለቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ገዳም የእርሻ ትራክተር አበረከተ።

ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ገዳም በአማራ ክልል አዊ ዞን ከዳንግላ ከተማ በምዕራብ አቅጣጫ 18 ኪ.ሜ ወንደፋይ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል።

ወለተ ጴጥሮስ አንድነት ገዳም በዐፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት በጻዲቋ ወለተ ጴጥሮስ የተመሰረተች ጥንታዊትና ታሪካዊት ገዳም ናት፡፡ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ በማኀበራዊ ሚዲያ ላይ በማስተባበር የገዳሟን አንዱ ችግር የሆነውን የእርሻ ትራክተር ገዝቶ አበርክቷል።

በማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰሩ እንደዚ አይነት መልካም ስራዎች ሊበተታቱ ይገባሉ።
    https://t.me/+zsQENK1iuHYzMDFk
https://t.me/+zsQENK1iuHYzMDFk
3.8K views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 20:10:15
      #ጥንቃቄ_ይደረግ !!

የምስራቅ አማራ ፋኖ ነኝ የሚለዉን ሀይል  ልብስ የለበሱ 4 የወራሪዉ ሀይል  ሰርጎ ገቦች፤  ወደ ግንባር  እየሄድን ነዉ በማለት ጥቁሩን አስፋልት ይዘው ወደ ሰሜን ወሎ ሲጓዙ በአምባሰል ወረዳ #ጎልቦ ከሚባል አካባቢ በቁጥጥር ስር ዉለዋል ።
     ራያ ቆቦ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.2K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 19:55:42
ሰበር ዜና!!!
በተለያየ አቅጣጫ ውጊያ የከፈተው ህውሀት በሱዳን ድምበር ሀምዳይት፣ በአበርግሌ፣ በአደርቃይ፣ በራያ፣ በወርቄ በሁሉም ግምባር የተሰለፈው መንጋው በኢትዮጵያ ጥምር ጦር ተደምስሷል!!

ምሽጎች ነጭድንጋይ፣ አዘዛ፣ ሸረሪማ.. በሱዳን ግምባር ተደርምሰው በኢትዮጵያ ጥምር ጦር ቁጥጥር ስር ውለዋል። የተረፈው መንጋ እየተሳደደ ይገኛል። ይህ በእንደህ እንዳለ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ሰራዊቶች ከመከላከል ወደ መልሶ ማጥቃት በመሸጋገር ተከዜን ተሻግሮ ወደ ደደቢትና በአበርግሌ ሳምሪ ተሸጋግረዋል።

በሌላ ዜና አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይና አልባኒያ የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ እንዲወያይ ለሀሙስ ስብሰባ መጥራታቸው ተሰምቷል።

    @ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.5K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 19:27:27
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ግምቱ ከ500 ሺህ ብር በላይ የሚሆን ስንቅ አዘጋጁ

የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሀገራችንን ለሚጠብቀው መከላከያ ሀይላችን ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብን በሚል ተነሳሽነት የስንቅ ዝግጅቱን የጀመሩት ነዋሪዎቹ መንግስት ሳይፈልግ ተገዶ የገባበትን ጦርነት በድል እስኪያጠናቅቅ ድረስ በሁሉም ግንባር ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል

በስንቅ ዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ነዋሪዎቹን ያበረታቱት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ብሩክ ከድር ህዝቡ ላደረገው ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበው ይህ የሚያሳየው ለሀገራችሁ ሉዓላዊነት ህይወታችሁን ለመስጠትም ቢሆን የየተዘጋጃችሁ መሆናችሁን ነውና ኢትዮጵያ በታሪክ ስትዘክራችሁ ትኖራለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ተሸንፋ አታውቅም ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ለ3ኛ ጊዜ ተገደን የገባንበትን ጦርነትም በእናንተ ተደግፈን በድል እንወጣዋለን ለዚህ ደግሞ ያለፈው ታሪካችን ምስክር ነው ብለዋል።

በመከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ መደብሮችና ክበቦች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ታደሰ ታምሩ በበኩላቸው ነዋሪዎቹ በራሳቸው ተነሳሽነት እያደረጉ ላሉት ድጋፍ አመስግነው ኢትዮጵያዊ ፍቅር ያላችሁን እናንተን ይዘን የማንሻገር ችግር አይኖርምና አሁንም የተከፈተብንን ጦርነት በድል አጠናቀን የኢትዮጵያን ነፃነት የምናውጅበት ቀን ሩቅ አይደለም። ለዚህም በሰራዊቱ ስም ቃል እገባላችኋለው ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተዘጋጀው ስንቅ ግምቱ ክ500 ሺ በላይ ሲሆን በቀጣይም በሁሉም ግንባር ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሐኑ ሀይሉ ተናግረዋል

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.8K viewsedited  16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 18:46:02 ለገሐር አካባቢ በሚገኝ ህንጻ ምድር ቤት ውስጥ የአንድ ግለሰብ ህይወት አልፎ ተገኘ

በአዲስ አበባ በዛሬው እለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት 30 ደቂቃ ላይ ለገሐር አካባቢ በአንድ ህንጻ ምድር ቤት ስር የተጠራቀመ ውሃ ውስጥ በስፋራው የሚሰራ አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ህይወቱ ያለፈዉ ግለሰብ የ32 ዓመት ወጣት ሲሆን እየተገነባ ባለዉ ህንጻ  ላይ ሰራተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ከፍተኛ ባለሙያ ነበር። ትላንት ቀን ላይ በድንገት ከስራ ቦታዉ በመጥፋቱና ዛሬም ስራ ላይ ባለመገኘቱ ጥርጣሬ የገባቸዉ ሰራተኞች ዛሬ ለፖሊስ ሪፖርት አድርገዋል።

ፖሊስ በመጠራጠር አስከሬኑ እንዲፈለግ ለኮሚሽን መስሪያ ቤት ሪፖርት በማድረጉ አስከሬኑ በህንጻዉ የተለያዩ ስፍራዎች ሲፈለግ ቆይቶ በህንጻዉ ቤዝመንት በተጠራቀመ ዉሀ ዉስጥ ሊገኝ ስለመቻሉን ተገልፃል።

አስከሬኑን የእሳት አደጋ ባለሞያዎችና በቦታዉ ከነበሩ ሰራተኞችና የፖሊስ አባላት ጋር  በመተባበር አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በትግስት ላቀው

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.0K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 18:45:11 ከወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ውሳኔ

የከተማውን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ ከተማ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የሰዓት እላፊ ገደብ ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ክልከላዎችን ማስቀመጥ በማስፈለጉ የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ ምክር ቤት የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

1. ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ በከተማችን በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡

2. ከተፈቀደላቸው የመንግስት የፀጥታ አባላት ውጭ የሰራዊቱን አልባሳትን መልበስ የተከለከለ ነው፡፡

3. ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የከተማውን ማህበረሰብ የሚያውኩ አሉባልታዎችን በሚዲያዎችና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት በማሰራጨት ህዝቡን ማዋከብ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

4. በከተማችን የሚገኙ የራያና ቆቦ ከተማ ተፈናቃዮች ውጭ ሌላው አካል ወደ መጣበት አካባቢ እንዲመለስ በጥብቅ እናሳስባለን

5. በከተማችን የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤት፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ የንግድ ተቋማት እና የመሳሰሉትን መዝጋት ፍጹም የተከለከለ ነው፡፡

6. ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ለፀጥታ ስራ ትብብር ሲጠየቅ የመተባበር ግዴታ አለበት። ነገር ግን ተሸከርካሪን የሚሸሽግ፣ የሚያሸሽ፣ ሆን ብሎ ተበላሸ በሚል ላለመተባበር ጥረት የሚያደርግ ግለሰብ እና ድርጅት ተጠያቂ ይሆናል።

7. የመኖሪያ ቤትና የመኝታ አልጋ የሚያከራይ ግለሰብ የተከራዮቻችሁን ማንነት የመለየትና የታደሰ መታወቂያ ስለመያዛቸው የማረጋገጥ ግዴታ ሲኖርባችሁ አጠራጣሪ ጉዳይ ሲኖር ለጸጥታ አካል ሪፖርት የማድረግ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ በግልፅ እናሳስባለን

8. ፀጉረ ልውጥ ሰው የሚያገኝ ግለሰብ በቅርቡ ለሚገኝ የፀጥታ አካል የመጠቆምና የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል

9. ከነሀሴ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቀበሌ መታወቂያ መስጠት የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን።

10. ማንኛውም የመንግስት እና የግል ታጣቂ አካባቢውን በብሎክ አደረጃጀት ውስጥ በመካተት በየደረጃው ያለ የፀጥታ አካላት በሚሰጠው ስምሪት አካባቢውን የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት

11. አግባብነት የሌለው የዋጋ ንረት መፍጠር፣ በሸቀጦችና በግብርና ምርቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጨምሮ ህዝቡን ማስቃየት፣ በማንኛውም ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ መገኘት በህግ ያስጠይቃል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች ማንኛውም አካል የማክበርና ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ ያለበት መሆኑንና ይህን ውሳኔ የማያከበር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ በአጽእኖት እናሳውቃለን፡፡


የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት

ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም

ወልድያ


@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.9K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 18:44:53
ሩዋንዳ 0-1 ኢትዮጵያ

(22' ዳዋ ሆቴሳ)

ኢትዮጵያ በአልጄርያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ማለፋን አረጋገጠች።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.8K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ