Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.66K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 215

2022-09-02 19:54:47 #Update

#ወልድያ

ሰሞኑን በአሉባልታና ሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ የተወሰነ አለመረጋጋት ውስጥ የነበረችው ወልድያ ዛሬ ወደ ቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሷ ተገልጿል። ከከተማዋ ወጥተው የነበሩም ተመልሰዋል። መደበኛ ትራንስፖርት ፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች የመንገድ ዳር አገልግሎቶች ጀምረዋል።

ዛሬ ጥዋት ላይ አቢሲንያ እና ህብረት ባንኮች ስራ መጀመራቸው እና ሌሎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል ፤ በዚሁ መሰረት ከሰዓት በከተማው ውስጥ ያሉ ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

#ደሴ

ደሴ ከተማ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለች ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ በመራቅ ሰላሙን ሊያስጠብቅ ይገባዋል። በሀሰተኛ መረጃ አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

#ኮምቦልቻ

ዛሬም እንደትላንቱ ኮምፖልቻ ከተማ እና ነዋሪዎቿ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሆኑ አሁንም ነዋሪው ተረብሾ አካባቢውን ለቆ ፣ ንብረቱን ጥሎ እንዲወጣ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና አሉባልታዎች ሊኖሩ ይችላሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

#ሐይቅ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተሰራጨ የሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን የመመለስ ስራ በከተማው አስተዳደር እየተሰራ ነው። በተጨማሪ በከተማው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲሁም የኬላ ላይ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን መላው ነዋሪ የወጡትን ክልከላዎች እና ገደቦች እንዲያከብር ተጠይቋል።

#ሸዋሮቢት

በትላንትናው ዕለት " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች የተገደሉት የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
4.1K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 19:37:03
ለጥንቃቄ

የአሸባሪው ህወሃት አዲሱ ድራማ ..!!!

ወራሪው ሃይል በልብስ ባለሞያዎች ቀይ ቦኔት በማሰራት ከሰሜን እዝ ያፈናቸውን ታፋኞች አልብሶ ቀይ ቦኔት ለባሽ ኮማንዶ ማረኩኝ ለማለት አዲስ ፕሮፓጋንዳና ድራማ ወደ ሚዲያ ለማስገባት ከፍተኛ ቀረፃዎች እያካሄደ ይገኛል። ሰሞኑን ሚዲያውን ለማጥለቅለቅ እየተዘጋጁ መሆኑን መረጃ ደርሶኛል ምናልባት ፕሮፓጋንዳው እውነት እንዳይመስላችሁ።

ህወሃት ይሄን ለማድረግ የፈለገው ቀይ ቦኔት ለባሽ ኮማንዶ ምን ያህል እንደሚቀጠቅጠው በሚገባ ስለ ተረዳ የስና ልቦና ውጊያ ለማድረግ እና ድራማዎቹ ሁሉ ስለተነቃባቸው ነው።

ሼር ይደረግ

የኢትዮጵያ ሰራዊት በወንበዴ ድራማ ስሙ የሚጠፋ ሞራሉ የሚነካ አይደለም

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.8K views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:49:23
የሸዋሮቢት ከንቲባ ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ!

የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው አሁን ከመሸ 3:00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሀይሎች ጥቃት ተፈፅሞበት ህይወቱ እንዳለፈ መረጃ ደርሶናል።

ነፍስ ይማር!
2.0K views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:59:37
#በዋግኽምራ ግምባር
ዛሬ በዚዝ ግምባር በተደረገው ጦርነት መከላከያ ሰራዊት የጁንታውን ኃይል በመደምሰስ ጁንታው ይጠቀምበት የነበረውን ዋሻ ሲፈተሽ የተገኘ ነው።

ለተረጂ ህዝብ የተላከ የእርዳታ ምግብ ለጦርነት እየተጠቀመው መሆኑን ግልፅ ማሳያ...ነው

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:58:27
መረጃ

ወራሪው የህወሓት ጉጀሌ በወልዲያ ይዞት የነበረውን ተራራ ሙሉ በሙሉ እየተገረፈና እየረገፈ  ዛሬ ወዶ ሳይሆን ተገዶ ለቋል። ክብር ለጥምር ጦሩና በተለይ ለባለ ቀይ መለዮ ኮማንዶዎች::

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.5K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:46:04
ጉባኤው በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ በመግለጫው የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ አሁንም የሰላም ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ጥረቱ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሁሉ ሌሎችም ወገኖች ለዚሁ መልካም ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ እንዲደረግላቸውም አሳስበዋል። ለወታደራዊ ዘመቻ ህፃናትን ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል ያለው ኢዜአ ነው። በአገራዊ ጉዳይ በተለይ ወጣቶች ሁኔታውን በጥልቀት በማጤን ከስሜት በወጣ፣ ነፃና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ እንዲመረምሩ ጠይቀዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:11:06
ጎጃም አመረረ ጎጄ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ አረ ማነው እኔ ፊት የሚቆመው ብሏል ዛሬ!

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.2K viewsedited  17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:40:59
አሁናዊ መረጃ ከስፍራው!

በወልቃይት በረከት እና ሉግዲ መሃከል ትናንት በረድ ብሎ የነበረው ጦርነት ዛሬ ሌሊት 9 ሰዓት በድጋሚ ጀምሮ እስከ ረፋዱ 3 ሰዓት ድረስ በከባድ መሳሪያ የታገዝ ጦርነት ተካሂዷል።

የትህነግ ጦር አስቀድሞ ከሰራቸው 5 ባለ ሶስት ደረጃ ምሽጎች ውስጥ ሶስቱ ተሰብረዋል። የተቀሩትም በቀጣይ 24 ሰዓታት ውስጥ እንደሚሰበሩ አሁን ያለው ጦርነት ምስክር ነው። መከላከያ ሰራዊቱ እና ልዮ ኃይሉ በጥምር እያጠቁ ነው። ከሁመራ ከተማ 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው ጦርነቱ በማይካድራ አቅጣጫ እየተካሄደ ያለው።

ፋኖ፣ሚሊሻውና የአካባቢው ታጣቂ በቅርብ እርቀት ላይ ቢሰፍርም እስካሁን እንዲገባ አልተፈቀደም። ማይካድራን ጨምሮ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ከተማ ሁመራ በፋፁም መረጋጋት እና ሰላም ትገኛለች።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.3K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:16:21
ሰበር ዜና!

በራያ ግምባር አሁን #ጎብየ በጀግናው የመከላከያ፤የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ጥምር ጦር ነጻ ሁናለች! ይቀጥላል ...!

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.2K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 18:28:06
#Update
ቤተል አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ 4.7 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ወድሟል

አደጋውን ለመቆጣጠር በተደረገ ርብርብ 100 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለብስራት ኤፍኤም አስታውቋል። አደጋዉን ለመቆጣጠር 4 ሰዓት በፈጀው ርብርብ ስድስት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹን ለማገዝ የተሳተፉ አምስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል። የአደጋውን መንስኤ አሁንም ፖሊስ እያጣራ ይገኛል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.2K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ