Get Mystery Box with random crypto!

#Update #ወልድያ ሰሞኑን በአሉባልታና ሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ የተወሰነ አለመረጋጋት ውስጥ የ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

#Update

#ወልድያ

ሰሞኑን በአሉባልታና ሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ የተወሰነ አለመረጋጋት ውስጥ የነበረችው ወልድያ ዛሬ ወደ ቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሷ ተገልጿል። ከከተማዋ ወጥተው የነበሩም ተመልሰዋል። መደበኛ ትራንስፖርት ፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች የመንገድ ዳር አገልግሎቶች ጀምረዋል።

ዛሬ ጥዋት ላይ አቢሲንያ እና ህብረት ባንኮች ስራ መጀመራቸው እና ሌሎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል ፤ በዚሁ መሰረት ከሰዓት በከተማው ውስጥ ያሉ ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

#ደሴ

ደሴ ከተማ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለች ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ በመራቅ ሰላሙን ሊያስጠብቅ ይገባዋል። በሀሰተኛ መረጃ አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

#ኮምቦልቻ

ዛሬም እንደትላንቱ ኮምፖልቻ ከተማ እና ነዋሪዎቿ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሆኑ አሁንም ነዋሪው ተረብሾ አካባቢውን ለቆ ፣ ንብረቱን ጥሎ እንዲወጣ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና አሉባልታዎች ሊኖሩ ይችላሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

#ሐይቅ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተሰራጨ የሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን የመመለስ ስራ በከተማው አስተዳደር እየተሰራ ነው። በተጨማሪ በከተማው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲሁም የኬላ ላይ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን መላው ነዋሪ የወጡትን ክልከላዎች እና ገደቦች እንዲያከብር ተጠይቋል።

#ሸዋሮቢት

በትላንትናው ዕለት " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች የተገደሉት የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA