Get Mystery Box with random crypto!

'...የትግራይን ጨቅላ ህፃናት ከከንቱ እልቂት የመታደግ ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታ አለብን ነው ያልነው | ሰበር ዜና ET🇪🇹

"...የትግራይን ጨቅላ ህፃናት ከከንቱ እልቂት የመታደግ ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታ አለብን ነው ያልነው" :- የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገራዊና ህዝባዊ ኃላፊነቱን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየፈፀመ መሆኑን ገለጸ!!


መከላከያ ሠራዊት ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው አሸባሪው ህወሓት የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱ፣ እኔ እየመራሁ የማልዘርፋት ሀገር ትፍረስ እኩይ ተግባሩና ፀረ ህዝብ ባህሪው አንፃር የሚጠበቅ ነው። በተቃራኒው እኛ ግን የመላው 120 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵውያን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ተቀብለን የምንፈፅም ህዝባዊና ፕሮፌሽናል ብሔራዊ ኃይል ስለሆንን መላውን ህዝባችንና የትግራይን ጨቅላ ህፃናት ከከንቱ እልቂት የመታደግ ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታ አለብን ነው ያለው፡፡

ስለሆነም መከላከያ ሰራዊት ህግን ተከትሎ ወገኑን ከሰቆቃና እልቂት ለመታደግ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት በጀግንነት በመክፈል የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም ያስከብራል ነው ያለው፡፡

ስለሆነም መከላከያ ሰራዊት ህዝባችንን ከዚህ አሬመኔ ቡድን ቀንበር ለማላቀቅና ከከንቱ ጭፍጨፋ ለማዳን ህዝባችንና ለሀገራችን ይጠቅማል የተባለውን ሁሉ በመስዋዕትነታችን እውን ለማድረግ በከፍተኛ ብቃትና የላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

እኛ ታላቅና ታሪካዊ ኃላፊነት ካለበት የመከላከያ ኃይል በሚጠበቅ አግባብ፣ ሁለተናዊ በሆነና ነገን አሻግሮ በሚመለከት እሳቤ እንዲሁም በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የምናደርገው እና እናንተ በጋለ ጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት ዛሬ፣ አሁን፣ እዚችው እዲሆን የምትፈልጉትን ሁሉ "አፍ በእጅ በሚያስይዝ" አስተማማኝና ዘላቂ በሆነ ድል ይታረቃል ሲልም አረጋግጧል፡፡
 
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA