2023-04-18 08:50:21
#sudan_news
በሱዳን የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ተደበደበ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብረት ለበስ ተሽከርካሪው " ሆን ተብሎ " በጥይት መደብደቡን ኢምባሲው ያስታወቀ ሲሆን ድርጊቱን የፈፀመው ሄሜቲ የሚመሩት RSF ቡድን መሆኑን ኤምባሲው ለአል አረቢያ ገልጿል።
ኤምባሲው ተሽከርካሪው በ100 ጥይት መደብደቡን ገልጾ ድብደባው ያደረሰው ምንም ጉዳት የለም ብሏል።
በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን ዜጎቹን የማስወጣት እቅድ እንደሌለው ዋይትሃውስ አሳውቋል።
በተያያዘ ዜና በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰምቷል ።
አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።
ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።
የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።
ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ #አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።
ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።
ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
358 views05:50