Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-18 19:14:18 “ከራያ አላማጣ ህዝብ ፍላጎት ውጪ የሚመጣ ማንም የህወሓት አመራር ወደ አላማጣ አይገባም”። ወደ ከተማዋ ደፍረው ቢገቡም የሚጠብቃቸውን እርምጃ ያውቁታል ብለዋል።
ወያኔና የወያኔ ደጋፊ ወደ አካባቢያችን ቢመጣ ፍርድ የሚያገኘው ከራያ ወጣት እንጂ ከሌላ አካል አደለም።
ወያኔና የወያኔ ደጋፊ ጥይት ታጥቆ በር ተኽላይን አይሻገርም።
አሁን ያለው የግዚያዊ አስተዳደር መዋቅር የሚነሳው ህዝበ ውሳኔ የሚካሄድ ከሆነ በህዝበ ውሳኔ ወቅት ብቻ ነው።
አሁን ያለው ግዚያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት አውቆት ይሁንታ ሰጥቶትና በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት እንጂ በጉልበት እንዳልሆነ ሁሉም ልያውቀው ይገባል።
የወያኔ አመራር ዳግም አላማጣ የሚረግጠው የሰራውን ወንጀል አምኖ እጁን ለካቴና ለመስጠት እንጂ አከባቢውን ለመምራት አይመጣም ።
ወያኔ የሰላም ስምምነቱ ጥሶ ድጋሚ ጦርነት አነሳለሁ በር ተኽላይን እሻገራለሁ ካለ ጠቡ ከጀግናው ሀገር መከላከያ ጋር እንጂ የራያ ወጣት ጋር አይሆንም(አዩዘሀበሻ)።
-የአላማጣ ከተማ ከንቲባ እና የወሎ ራያ አማራ ወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሃይሉ አበራ
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.1K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 19:13:58 በትግራይ ክልል ያሉ የመንግስት ሰራተኞች፤ በአስር ቀናት ውስጥ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ተላለፈ
በትግራይ ክልል መንግስት ስር ባሉ መዋቅሮች ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች፤ በአስር ቀናት ውስጥ በየመስሪያ ቤቶቻቸው ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ተላለፈ። በክልሉ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች፤ ውዝፍ የሶስት ወር ደመወዝ ክፍያ መሰጠት መጀመሩም ተገልጿል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የትግራይን ክልልን ተቆጣጥሮ የቆየው የመከላከያ ሰራዊት፤ የመቐለ ከተማን ለቅቆ ከወጣበት ከሰኔ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች መደበኛ ስራ አቁመው ቆይተዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሰብለ ካህሳይ፤ መደበኛ ስራ ተቋርጦ በቆየበት ጊዜ የክልሉ መንግስት ሰራተኞች በመስሪያ ቤቶቻቸው ይገኙ የነበረው ወጥ ባልሆነ ሁኔታ እንደነበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

“ፕሮግራም ወጥቶ ነበር ሰራተኛ ወደ ቢሮ ይገባ የነበረው። በሳምንት አንድ ቀንም [የሚገባ ነበር]። አንዳንድ ስራ የበዛበትም፤ ግማሽ ግማሽ ቀን ነው ስራ ይገባ የነበረው” ሲሉ ላለፉት አንድ ዓመት ከስምንት ወር ገደማ የነበረውን የስራ ሁኔታ አስረድተዋል። የፌደራል መንግስት እና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ በተፈራረሙት የሰላም ስምምነት መሰረት ባለፈው መጋቢት ወር አጋማሽ ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙን ተከትሎ፤ ሰራተኞችን በመደበኛ ሁኔታ ወደ ስራ የማስገባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ኮሚሽነሯ አስታውቀዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.0K viewsedited  16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 18:17:25 በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ
በጦርነቱ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መድረሱ ተገልጿል
ከተቀሰቀሰ አራተኛ ቀኑን በያዘዉ የሱዳን የከተማ ዉስጥ ጦርነት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና የአገሪቱ ጦር ዉግያ ዉስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ በሆነችዉ ሱዳን ኢትዮጵያዊንም ህይወታቸዉ እንዳለፈ ተሰምቷል።

በሱዳን 12 ዓመታትን የቆየዉና አስተያየቱን ለብስራት ራዲዮ የሰጠው የጤና ባለሙያ ወንድወሰን ጌትነት፤ ከትናንት በስቲያ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ኦምዱርማን በተሰኘዉ አካባቢ በጦርነቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን በጦር ጄት ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ተናግሯል። እስካሁን ከ10 በላይ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ ሞተዋል ያለም ሲሆን፤ በትናትናዉ ዕለት በካርቱም ( ጅሬፍ ) በደረሰ ሌላ ጥቃት፤ ባለትዳሮች ሕይወታቸውን ሲያጡ የሦሥት ዓመት ሕጻን ልጃቸዉ ከጥቃቱ መትረፉን ገልጿል።

በተጨማሪም በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይም ጥቃት መድረሱን የገለጸው ወንድወሰን፤ የትኞቹ ታጣቂዎች እንደፈጸሙት ባያረጋግጥም የኤምባሲዉን ቅጥር ግቢ ጥሰዉ በመግባት በግቢዉ በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባለቤት በሆነበት የመጠለያ ማዕከል ዉስጥ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ አጸያፊ ተግባራት ጭምር መፈጸማቸዉን ተናግሯል።

የኤምባሲዉ ጥበቃዎች በጦርነቱ ወቅት ከግዳጅ ቦታቸዉ በመነሳታቸዉ የተባለዉ ጥቃት መድረሱንና፤ ታጣቂዎቹ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ዘረፋዎችን መፈጸማቸዉንም ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን ልዩ ተወካይ ባወጣው መረጃ፤ በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት እስከ አሁን በትንሹ 200 ሰዎች መሞታቸው የገለጸ ሲሆን፤ 1 ሺሕ 8 መቶ ያህል ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸዉን አስታውቋል፡፡
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.3K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 17:08:54 የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጡ ሰብአዊ መብት የሚጥስ ነው ሲል አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በተመረጡ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለዉን ማዕቀብ እንዲያነሳም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠይቋል።

አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት እገዳዉን ከጣለ 3ኛ ወሩን ይዟል።

እገዳዉ ሰዎች መረጃ እንዳያገኙ መገደብን ጨምሮ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና ያለመጠቀም የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነዉ ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዉሞን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብትን እንዲያከብርና የታሰሩ የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን እንዲፈታ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ትናንት ማምሻ ባወጣዉ መገለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት አማራ ክልል በተፈጠረዉ ሁከት ምክንያት ያሰሯቸዉን 7 የመገናኛ ዘዴ ባልደረቦች ባስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ከእስረኞቹ ባንዷ ላይ ተፈፀመ የተባለዉን አካላዊ ጥቃት እንዲያጣሩ ጠይቋል።

መግለጫዉ  እንዳለዉ  ባለስልጣናቱ «ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና ሁሉም ወገን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብቱን ማስከበር አለባቸዉ።

»ባለፈዉ ሳምንት በአማራ ክልል የመብት ጥሰትና ሁከት መቀስቀሱ እንዳሳሰበዉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታዉቋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉ፣ የሰብአዊ ርዳታ አቀባይ ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ ሰዎች መገደላቸዉ፣ አዲስ አበባ ዉስጥ ሰዎች በጅምላ መታሰራቸዉንም ድርጅቱ «አሳሳቢ» ብሎታል።

የመንግስት ኃይላትም ሆኑ ሌሎች ታጣቂዎች «የሰብአዊ ርዳታ ሰራተኞችን ያለማጥቃት ኃላፊነት አለባቸዉ።» ይላል መግለጫዉ።
@ET_SEBER_ZENA
2.5K viewsedited  14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 15:20:06
Inbox #ደቡብ
ሰላም ስለታማኝ መረጃዎቻቹ ከልብ አመሰግናለው።
እኔ ዛሬ በቤተሰብ ሀዘን ምክንያት ወደ ደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን በመጓዝ ላይ ነበርኩ ልክ አዲሎ አከባቢ ስንደርስ ባደዋቾ ላይ የመንግስት መምህራን የ3 ወር ደሞዝ አልተከፈለንም በማለት ከአዲስ አበባ ከአዳማ ከሻሸማኔ ወደ ሾኔ እና ወላይታ የሚጓዙ መንገደኞች በመምህራን ተቃውሞ ምክንያት ተስተጓጉለው ውለዋል።
ይህን መረጃ ለሚመለከተው አካል አድርስልን።
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.8K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 15:19:15
መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ የሚመሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለተጓዦች ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ለመክፈትና ለሰብአዊ እርዳታ የ24 ሰዓት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምቷል፡፡ ይህንኑ መሪው ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄምቲ ገልጸዋል፡፡ ሄሜቲ ከአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ እና ወዳጅ ካሏቸው አገራት ጋር ንግግር ከተደረገ በኃላ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡ ስለ ስምምነቱ እየተወራ ባለበት ወቅት በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሚገኘውን የወታደራዊ ዋና መስሪያ ቤት ለመቆጣጠር በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ አሁንም ድረስ እየተካሄደ ነው።
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.7K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 12:39:08 Inbox
ሰላም ሰበር ዜና ET በቅድሚያ ለምትሰጠን ፈጣን መረጃ በእጅጉ እያመሰገንኩ፣ትናንት በአዋሽ ፓርክ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሼኔ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው ሁለት ሰዎችን በፅኑ አቁስለው አንድ ሰው አፍነው ወስደዋል። ይሄ የሆነው ልዩ ሀይሉ ትጥቅ መፍታቱን ተከትሎ በተፈጠረ ክፍተት ነው፣መከላከያ ሰራዊት ወደ ቦታው ስምሪት ሊሰጠው ይገባል።
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.0K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 12:37:14 የሱዳን ጦር ተቆጣጥሮት የነበረውን የኢትዮጵያ መሬት ለቆ ወደ ካርቱም ሄዷል አየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ከአውድ ውጪ የሆነ መረጃ ነው።
ለምሳሌ ስናር፣ሰላምበር እና አቡኪር በሚባሉ የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በስፋት አሰሳ እያደረጉ እንደሆነ ከታማኝ ምንጭ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.9K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 12:36:17
ማስተካከያ
"ስጋ ከድመት ለማስጣል ስትሞክር ህይወቷ አለፈ" የተባለችዉ ወጣት ታሪክ የተሳሳተ መሆኑን ቤተሰቦቿ ተናገሩ
በቀለች ደስታ የተባለች የ 18 አመት ወጣት ሚያዝያ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባጋጠማት የኤሌክትሪክ አደጋ ህይወቷ ማለፉ ተሰምቷል። በወቅቱ ወጣቷ ህይወቷ አልፏል የተባለበት ምክኒያት ከድመት ስጋ ለማስጣል ስትሞክር ነዉ ተብሎ የተሰራጨዉ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን መረጃዉ እንዲስተካከልልን እንፈልጋለን ያሉ አደጋዉ ባጋጠመበት ሰዓት በአካባቢው የነበሩ ሰዎች እና የአሳዳጊ ቤተሰቦቿ የቅርብ ሰዎች ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
የ 10 ኛ ክፍል ተማሪ የነበረችዉ በቀለች ፤ ለእርድ በመዘጋጀት ላይ ለነበረ በግ በተለምዶዉ ሜንጦ የተሰኘዉን የእርድ መሳሪያ ጣሪያ ላይ ለመስቀል ባደረገችዉ ሙከራ አደጋዉ ማጋጠሙን በወቅቱ በቦታዉ ላይ የነበሩትና የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዘዉዴ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
"እርዱም አልተከናወነም ፤ በሀገራችን ድመት የነካዉን ስጋ መመገብ ጸያፍ ነዉ ያሉት " አቶ ተስፋዬ መረጃዉ በተሳሳተ መልኩ መሰራጨቱ ቤተሰቦቿንም ሆነ ጎረቤቶችን ያሳዘነ መሆኑን ተናግረዋል።
ሌላዉ የቅርብ ጎረቤት የሆኑት ወ/ሮ ትግስት ጌታቸዉ ሁኔታዉን እንደገለጹት ፤ በወቅቱ የአካባቢዉ ፖሊስም በቦታዉ ከነበሩ ሰዎች ይህንኑ ቃል መቀበሉን የገለጹ ሲሆን በአዲስአበባ ፖሊስ በኩል ግን ይህን መሰል መረጃ መሰራጨቱ አሳዝኖናል ብለዋል።
የወጣቷ ቀብር በቤተሰቦቿ መቀመጫ በአንጎለላ እና ጠራ ወረዳ በጫጫ ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ አካባቢ በትናንትናው እለት መፈጸሙን ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
#ዳጉ_ጆርናል
ነፍስ ይማር
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.8K views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 12:35:07 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ አማራ የሆኑ የብልፅግና አባል የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች መታሰራቸው ታውቋል። በተለይ በንፋስ ስልክ ክፍለተማ ብዙ አመራሮች ታስረዋል። እስካሁን ከ14-15 የሚደርሱ አመራሮች ታስረዋል። ለእስር የተዳረጉበት ምክንያትም የፋኖ ደጋፊ ናችሁ፣ፅንፈኛ ናችሁ እንዲሁም በሙስና ተጠርጥረው እንደታሰሩ እና እስካሁን ፍርድ ቤትም አልቀረቡም።
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ