Get Mystery Box with random crypto!

ማስተካከያ 'ስጋ ከድመት ለማስጣል ስትሞክር ህይወቷ አለፈ' የተባለችዉ ወጣት ታሪክ የተሳሳተ መሆ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

ማስተካከያ
"ስጋ ከድመት ለማስጣል ስትሞክር ህይወቷ አለፈ" የተባለችዉ ወጣት ታሪክ የተሳሳተ መሆኑን ቤተሰቦቿ ተናገሩ
በቀለች ደስታ የተባለች የ 18 አመት ወጣት ሚያዝያ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባጋጠማት የኤሌክትሪክ አደጋ ህይወቷ ማለፉ ተሰምቷል። በወቅቱ ወጣቷ ህይወቷ አልፏል የተባለበት ምክኒያት ከድመት ስጋ ለማስጣል ስትሞክር ነዉ ተብሎ የተሰራጨዉ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን መረጃዉ እንዲስተካከልልን እንፈልጋለን ያሉ አደጋዉ ባጋጠመበት ሰዓት በአካባቢው የነበሩ ሰዎች እና የአሳዳጊ ቤተሰቦቿ የቅርብ ሰዎች ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
የ 10 ኛ ክፍል ተማሪ የነበረችዉ በቀለች ፤ ለእርድ በመዘጋጀት ላይ ለነበረ በግ በተለምዶዉ ሜንጦ የተሰኘዉን የእርድ መሳሪያ ጣሪያ ላይ ለመስቀል ባደረገችዉ ሙከራ አደጋዉ ማጋጠሙን በወቅቱ በቦታዉ ላይ የነበሩትና የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዘዉዴ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
"እርዱም አልተከናወነም ፤ በሀገራችን ድመት የነካዉን ስጋ መመገብ ጸያፍ ነዉ ያሉት " አቶ ተስፋዬ መረጃዉ በተሳሳተ መልኩ መሰራጨቱ ቤተሰቦቿንም ሆነ ጎረቤቶችን ያሳዘነ መሆኑን ተናግረዋል።
ሌላዉ የቅርብ ጎረቤት የሆኑት ወ/ሮ ትግስት ጌታቸዉ ሁኔታዉን እንደገለጹት ፤ በወቅቱ የአካባቢዉ ፖሊስም በቦታዉ ከነበሩ ሰዎች ይህንኑ ቃል መቀበሉን የገለጹ ሲሆን በአዲስአበባ ፖሊስ በኩል ግን ይህን መሰል መረጃ መሰራጨቱ አሳዝኖናል ብለዋል።
የወጣቷ ቀብር በቤተሰቦቿ መቀመጫ በአንጎለላ እና ጠራ ወረዳ በጫጫ ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ አካባቢ በትናንትናው እለት መፈጸሙን ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
#ዳጉ_ጆርናል
ነፍስ ይማር
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA