Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-21 12:08:06
የኢትዮጵያ አምዶች በአገዛዙ እየተፈረካከሱ ባሉበት ሁኔታ ብልጽግናንን ከቦ እያሸበሸበ ካለ ፓርቲ ጋር መቀጠል አልችልም"።አቶ አንዷአለም አራጌ የቀድሞ የኢዜማ ም/ል መሪ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.2K views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 11:23:18
ወደ ትግራይ ክልል የታሰበው ጉዞ ተራዘመ
በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የሰላም ልኡክ መግለጫ ሰጠ።
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር በትግራይ በሚገኙ አኅጉረ ስብከት መካከል የነበረው ግንኙነት መቋረጡ ያወሳው መግለጫ በትግራይ ክልል የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በትግራይ ከልል ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች የግንኙነት ማስቀጠያ ደብዳቤዎች ሲጻፉ መቆየታቸውን ገልጿል።

ልኡኩ የደብዳቤው ግንኙነት እንደታሰበው የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከምዕመናን የተወጣጣ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን በመግለጫው ጠቅሷል።

የኮሚቴው ዓላማ የሰላም መድረክ ማመቻቸት፣ የምንቀራረብበትና  አንድ የምንሆንበትን መንገድ በጋራ ማፈላለግ ነው ያለው ልኡኩ ከጉዞ ጋር በተያያዘ ማሟላት ያሉባቸውን ጉዳዮች ለማሟላት ሲባል ከሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ሊደረግ የነበረውን ጉዞ ማራዘሙን ገልጿል። 

ልኡኩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ክልል ትግራይ በመጓዝ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓም በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።

EOTC TV
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.3K viewsedited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 08:38:18 አሜሪካ ከሱዳን ጦርነት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጦር ወደ ጂቡቲ ልትልክ ነው ተባለ
አሜሪካ ከሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጦር ወደ ጂቡቲ ልትልክ እንደሆነ ተነግሯል።

ወደ ጂቡቲ የሚላከው ጦር በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት የሚከታተል እና አሜሪካ ዜጎቿን ከሱዳን ማውጣንተ በሚያስፈልግበት ወቅት ድጋፍ የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ቅዳሜ እለት በሱዳን ጦር ኃይሎችእና በፈጥኖ ደራሽ ሰራዊቱ (አርኤስኤፍ) መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም፣ አጎራባች በሆነችው ኦምዱርማን እና በሌሎችም አካባቢዎች ከባድ ውጊያ አለ።

የዓለም ጤና ድርጅት የሱዳን ጤና ጥበቃ ሚንስቴርን ጠቅሶ እንዳለው በቅጭቱ 300 ገደማ ሰዎች ሲገደሉ፤ ከ2 ሽህ 600 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።AlAin
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.5K viewsedited  05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 08:14:31
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ከአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ጋር ለድርድር አልቀመጥም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ግጭቱን የጀመሩት ጀኔራል ቡርሃን ናቸው ያሉት ጀኔራል ደጋሎ፣ ወደፊትም ከባላንጣቸው ጋር ድርድር እንደማይኖር መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የሱዳን ጦር ሠራዊትም፣ ከፈጥኖ ደራሽ ሠራዊቱ ጋር የሚደረግን ድርድር ውድቅ አድርጓል። ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ጥሪ ብናደርግም የጦር ሠራዊቱ አዛዦች ግን ተኩስ አቁም አይፈልጉም ያሉት ጀኔራል ደጋሎ፣ ነገ ለሚከበረው ኢድ አልፈጥር በዓል ተኩስ አቁም ቢደረግ ተቃውሞ የለንም ማለታቸው ተገልጧል። ጀኔራል ደጋሎ ሠራዊታቸው ከሩሲያው የግል ወታደራዊ ኩባንያ "ዋግነር" ድጋፍ ያገኛል መባሉን አስተባብለዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 07:42:44
ሩሲያ “ደቡብ ኮሪያ ዩክሬንን ካስታጠቀች ሰሜን ኮሪያን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን አስታጥቃለሁ” ስትል ዛተች

ደቡብ ኮሪያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለመስጠት ሁኔታዎችን እየገመገመች መሆኑን ከሰሞኑ አስታውቃለች።

ህንን ተከትሎ ሩሲያ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ደቡብ ኮሪያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳትሰጥ አስጠንቅቃለች።

ደቡብ ኮሪያ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ ችላ ብላ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ከሰጠች ሞስኮ ለሰሜን ኮሪያ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እንደምታስታጥቅ ገልጻለች።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K viewsedited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 07:40:43
የሰበር ዜና ET አገልግሎት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ አል-አልፈጥር (ፈጥር) በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልጻል

ኢድሙባረክ !


@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.5K views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 21:43:33
Inbox #ከአላማጣ
ሰላም ሰበር ዜና ET በቅድሚያ ለፈጣን ወቅታዊ መረጃዎችህ በእጅጉ አመሰግናለሁ። የራያ አስመላሽ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ በማንነታቸው ለዓመታት በማይጨው እስርቤት ታስረው የነበሩ የራያ ልጆች ከእስር ተለቀው ዛሬ አለማጣ ከተማ ገብተዋል። በአስተዳደሩና ህዝቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የምሳ ግብዣም ተደርጎላቸዋል።
ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
1.8K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:27:19 የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ መሆኑ ታውቋል።

የሸዋል ወር ጨረቃ  በሳኡዲ አረበያ ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ጁምዓ / አርብ ይውላል።

እንኳን 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ምንጭ፦ Haramain Sharifain

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.7K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:04:27
የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት የዒድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ ማታ ከታየች ነገ አርብ ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ ይከበራል ሲል አሳውቋል

ይህን ያሳወቀው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ህብረተሰብ  የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለፀው ሼሪዓ ፍርድ ቤቱ  ሙስሊሙ ህብረተሰብ  በዓሉን ሲያከብር ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.9K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:03:58 አራት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በፌስቡክ ማንነቱን ቀይሮ በመተዋወቅ ‘‘ካናዳ እና እንግሊዝ እወስዳችኋለው’’ በማለት ጾታዊ ግንኙነት እንዲፈጽሙ አድርጓል የተባለው ግለሰብ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።

ግለሰቡ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ እና 20 ግራም ወርቅ ተቀብሎ የማታለል ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ነው በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የተወሰነው። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2ኛ አርቲዲ ወንጀል ችሎት ሲሆን÷ተከሳሹ ታዲዮስ ዘላለም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ነዋሪ ነው።

ተማሪዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጽ “ናቲ መላኩ” ብሎ ማንነቱን ቀይሮ በካናዳ ነዋሪ በመምሰል ከተዋወቃቸው በኋላ ‘’ካናዳና እንግሊዝ እወስዳችኋለው’’ ብሎ የማታለል ተግባር መፈጸሙ በክሱ ተመላክቷል። ከዚህም በኋላ ተከሳሹ ከካናዳ ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ በማስመሰል በግንቦትና በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም በተለያዩ ቀናቶች ለ4 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግል ተበዳዮች ስልክ ይደውላል፡፡ በዚህም'' ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጉዳይ የሚፈጽምላችሁ ሰው ይመጣል፤ አሻራ የሚወሰደው ከዘር ፈሳሽ እና ከወርቅ ስለሆነ አልጋ ይዛችሁ ጠብቁ በማለት'' የግል ተበዳዮች በተለያየ ቀናቶች በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አልጋ ይዘው እንዲጠብቁ ማድረጉ በክሱ ተጠቅሷል።

አልጋ እንዲይዙ ካደረገ በኋላ ማንነቱን ቀይሮ ወደ አልጋ ቤት በመሄድ የግብረስጋ ግንኙነት እንዲፈጽሙ ማድረጉም በክሱ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ተከሳሹ ከግል ተበዳይ ተማሪዎች ከእያንዳንዳቸው የተለያየ መጠን ያለው በአጠቃላይ 20 ነጥብ 7 ግራም ወርቅ ለአሻራ ምርመራ ያስፈልጋል ብሎ መውሰዱ በክሱ ተገልጿል፡፡ ለጉዳይ ማስፈጸሚያ በሚል ከእያንዳንዳቸው ግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ መቀበሉም በክሱ ተዘርዝሯል።

ተከሳሹ ከግል ተበዳዮች መካከል ከአንደኛዋ ተማሪ ጉዳይ ለማስፈጸም "አይፎን "ሞባይል ስልክ ያስፈልጋል በማለት እንድታመጣ በማዘዝ የስልክ ቀፎውን ለመቀበል በቀጠራት ዕለት ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ በኦፕሬሽን ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉ  በክሱ ተመላክቷል። በዚህም ተከሳሹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 692/1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በማታለል ወንጀል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦበታል።

ተከሳሹ ክሱ ከደረሰውና በችሎት በንባብ ከተሰማ በኋላ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲል የዕምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል። የፍትህ ሚኒስቴር የቦሌ ምድብ ዓቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዳሉ ያላቸውን የግል ተበዳዮችን ጨምሮ 6 ምስክሮችን በችሎት አቅርቦ የምስክርነት ቃላቸውን አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱ የምስክር ቃል መርምሮ ተከሳሹ ወንጀሉን መፈጸሙ በዐቃቤ ሕግ ምስክር ቃል ማረጋገጡን በመግለጽ ተከሳሹ በተከሰሰበት አንቀጽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ነበር። ይሁንና ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል ባለመቻሉ በመጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሰሰበት በአራት ክሶች በአንቀጽ 692 (1) ስር የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ተከሳሹ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉን ለህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ መፈጸሙን እንዲሁም ለማህበራዊ በጎ አድራጎት  ያበረከተውን አስተዋጾን የሚገልጽ   ከቦሌ ክ/ከ ወረዳ 13  ጽዳት አስተዳደርና ከዚሁ ወረዳ ከሴቶችና ሕጻናት ቢሮ የተሰጠውን ማስረጃ ጨምሮ  አራት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት አቅርቦ በፍርድ ቤቱ ተይዞለታል።

በዐቃቤ ሕግ በኩል ግን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት አለመቅረቡን የችሎቱ ዳኛ ገልጸዋል።

በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በደረጃ ስድስት በዕርከን 25 መነሻ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነ ሲሆን÷በዕርከን 3 መሰረት ደግሞ በ3 ሺህ ብር የገንዘብ እንዲቀጣ ተወስኗል። ቅጣቱን የአዲስ አበባ  ማረሚያ ቤት እንዲያስፈጽም የታዘዘ ሲሆን÷የቅጣት ውሳኔ ሲወሰን የግል ተበዳይ ከሆኑት ተማሪዎች መካከል ሁለቱ በችሎት ተገኝተው ቅጣቱን ተከታትለዋል።(በታሪክ አዱኛ)

  @ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.7K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ