Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ከአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ከአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ጋር ለድርድር አልቀመጥም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ግጭቱን የጀመሩት ጀኔራል ቡርሃን ናቸው ያሉት ጀኔራል ደጋሎ፣ ወደፊትም ከባላንጣቸው ጋር ድርድር እንደማይኖር መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የሱዳን ጦር ሠራዊትም፣ ከፈጥኖ ደራሽ ሠራዊቱ ጋር የሚደረግን ድርድር ውድቅ አድርጓል። ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ጥሪ ብናደርግም የጦር ሠራዊቱ አዛዦች ግን ተኩስ አቁም አይፈልጉም ያሉት ጀኔራል ደጋሎ፣ ነገ ለሚከበረው ኢድ አልፈጥር በዓል ተኩስ አቁም ቢደረግ ተቃውሞ የለንም ማለታቸው ተገልጧል። ጀኔራል ደጋሎ ሠራዊታቸው ከሩሲያው የግል ወታደራዊ ኩባንያ "ዋግነር" ድጋፍ ያገኛል መባሉን አስተባብለዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA