Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ ከሱዳን ጦርነት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጦር ወደ ጂቡቲ ልትልክ ነው ተባለ አሜሪካ ከሱዳን | ሰበር ዜና ET🇪🇹

አሜሪካ ከሱዳን ጦርነት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጦር ወደ ጂቡቲ ልትልክ ነው ተባለ
አሜሪካ ከሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጦር ወደ ጂቡቲ ልትልክ እንደሆነ ተነግሯል።

ወደ ጂቡቲ የሚላከው ጦር በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት የሚከታተል እና አሜሪካ ዜጎቿን ከሱዳን ማውጣንተ በሚያስፈልግበት ወቅት ድጋፍ የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ቅዳሜ እለት በሱዳን ጦር ኃይሎችእና በፈጥኖ ደራሽ ሰራዊቱ (አርኤስኤፍ) መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም፣ አጎራባች በሆነችው ኦምዱርማን እና በሌሎችም አካባቢዎች ከባድ ውጊያ አለ።

የዓለም ጤና ድርጅት የሱዳን ጤና ጥበቃ ሚንስቴርን ጠቅሶ እንዳለው በቅጭቱ 300 ገደማ ሰዎች ሲገደሉ፤ ከ2 ሽህ 600 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።AlAin
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA