Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ትግራይ ክልል የታሰበው ጉዞ ተራዘመ በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የሰላም ልኡክ መግለጫ ሰጠ። | ሰበር ዜና ET🇪🇹

ወደ ትግራይ ክልል የታሰበው ጉዞ ተራዘመ
በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የሰላም ልኡክ መግለጫ ሰጠ።
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር በትግራይ በሚገኙ አኅጉረ ስብከት መካከል የነበረው ግንኙነት መቋረጡ ያወሳው መግለጫ በትግራይ ክልል የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በትግራይ ከልል ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች የግንኙነት ማስቀጠያ ደብዳቤዎች ሲጻፉ መቆየታቸውን ገልጿል።

ልኡኩ የደብዳቤው ግንኙነት እንደታሰበው የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከምዕመናን የተወጣጣ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን በመግለጫው ጠቅሷል።

የኮሚቴው ዓላማ የሰላም መድረክ ማመቻቸት፣ የምንቀራረብበትና  አንድ የምንሆንበትን መንገድ በጋራ ማፈላለግ ነው ያለው ልኡኩ ከጉዞ ጋር በተያያዘ ማሟላት ያሉባቸውን ጉዳዮች ለማሟላት ሲባል ከሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ሊደረግ የነበረውን ጉዞ ማራዘሙን ገልጿል። 

ልኡኩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ክልል ትግራይ በመጓዝ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓም በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።

EOTC TV
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA