Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_seber_zena — ሰበር ዜና ET🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @et_seber_zena
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.85K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot
የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-10 11:59:16 የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ለመንግስት ሰራተኞች 45 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ አደረጉ
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ለመንግስት ሰራተኞች 45 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የደመወዝ ጭማሪውን ያደረጉት በፈረንጆቹ የፊታችን ግንቦት 14 ቀን የሚካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

የደመወዝ ጭማሪው ዝቅተኛ ተከፋይ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ ወደ 15 ሺህ የቱርክ ሊሬ ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡

ቀጣዩን ምርጫ ቢያሸንፉም የተከሰተውን የዋጋ ንረት በመንግስት ሰራተኞች ላይ ጫና እንዳይፈጥር አስፈላጊ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

ባለፉት 20 ዓመታት ቱርክን የመሩት ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በስልጣን ዘመናቸው በሀገሪቱ ታላላቅ ለውጦች ማስመዝገባቸውን አር ቲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.5K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 11:59:06
ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች በጂዳ እያደረጉት ያለው ድርድር እስካሁን ወደ ስምምነት የሚያመጣ ነገር እንዳልታየበት አለምዓቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ዛሬም በካርቱም ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ አለ።
ቡርሃን በበኩሉ የሀምዲቲ ጦር ካርቱምን ለቆ እስካልወጣ ድረስ ሰላም አይመጣም ማለቱን የሱዳን የዜና ምንጮች ዘግበዋል(አዩ)።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.3K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 11:58:52
በቀን ከ 10,000 ብር በላይ በወር ከ 300,000 ብር በላይ ያለ ምንም ልፋት ቤቶ ተቀምጠዉ ወደ ሀብት ማማ የሚጓዙበት ቀላል መንገድ

የሰዎችን አሸናፊ ትኬት በማየት ብቻ ሰሀቶትን አያቃጥሉ
አሁንም ጊዜዉ አልረፈደም ፈጥነው በመመዝገብ አብረዉን ወደ ስኬት ይጓዙ


 
https://t.me/+Vt82EQFPSAM2MTdk

https://t.me/+Vt82EQFPSAM2MTdk

https://t.me/+Vt82EQFPSAM2MTdk
2.4K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 06:55:56
የሐዘን መግለጫ

የአንደኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪያችን የነበረው ተማሪ አበባው ስንሻው መጸዳጃ ቤት ውስጥ ገብቶ የመጸዳጃ ቤቱን በር በመቆለፍ በራሱ ቀበቶ ራሱን አጥፍቶ በመገኘቱ ዩኒቨርሲቲያችን የተሰማዉን ጥልቅ ሐዘን ይገልፃል።

ተማሪው እዚህ አሳዛኝ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያበቁትን ጉዳዩች ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልግ ቢሆንም ፈተና ከበደኝ በሚል ሲጨናነቅ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ስለሆነም ለቤተሰቦቹ ፣ ለጓደኞቹና ለዩኒቨርስቲያችን ማህበረሰብ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን!
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.0K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 20:12:34
በሱዳን የተከሰተውን ግጭት በመሸሽ የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው
የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች መሆኑ ተነገረ።

ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች እንደገቡና ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ መተማ ዮሃንስ ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20 የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ ። በዚህ የጦርነት ስጋት ሽሽትም ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል።

የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሆነ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ገልፇል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.0K views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 16:31:21
ዛሬ ምሽት አራት ሰአት በኢትሃድ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ መዳረሻ የሚጠቁም እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ በማንቸስተር ሲቲና አርሰናል መሀከል ይደረጋል። ሲቲ ከመሪው አርሰናል በአምስት ነጥብ አንሶ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እያሉት እግር በግር አርሰናልን እየተከተለ ይገኛል።

አርሰናል ለመጨረሻ ግዜ ሲቲን ያሸነፈው በ 2020 በ ኤፍ ኤ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ነበር። ከዛ ቡኋላ በ ሁሉም ውድድሮች ሲቲን ማሸነፍ አልቻለም። ዛሬ በወሳኙ ጨዋታ ማን ድል ይቀናዋል? በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.8K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:25:52
ሳፋሪኮም 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈጽሟል።

በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት አልሚዎች የቴሌኮም መሠረተ ልማትን ከሀገር ውስጥ ኦፕሬተሮች የመከራየት አስገዳጅ አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል። ይኽም የኢትዮ ቴሌኮም የገበያ አቅምን ፈጥሯል። 

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ የግል የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዚሁ አስገዳጅ ሕግ መሠረት የራሱን የቴሌኮም መሠረተ ልማት መገንባት ስለማይችል የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት በኪራይ የመጠቀም ግዴታ ውስጥ ገብቷል።

በዚህም መሠረት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት መጠቀም የጀመረ ሲሆን፣ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥም ከኢትዮ ቴሌኮም ለሚያገኘው የመሠረተ ልማት መጋራት አገልግሎት 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ መፈፀሙን ሪፖርተር አስነብቧል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
3.1K viewsedited  10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:25:19
የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ
በድርጅቶች የሚከፈለው የኪራይ ገቢ ግብር መጣኔ 30% (ሰላሳ በመቶ) ነው፡፡
የተከራይ አከራዮች
የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው፡፡
ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡
የግለሰቦች የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ መጣኔዎች ከላይ በፎቶ የተጠቀሱት ናቸው።
ገቢዎች ሚኒስተር

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.8K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:25:12 በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ውይይት ትናንት ተጀመረ
በታንዛኒያ የሰላም ድርድር ዛሬ ማለዳ መጀመሩን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ስድስት ሰዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል ወደ ታንዛኒያ የተጓዘው የልዑካን ቡድን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግበዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል አንጋፋው የታሪክ ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዋና አዛዥ አማካሪ ሚስተር ጂሬኛ ጉዳታ እና አቶ አብዲ ጠሃ እና ሌሎችም መገኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.6K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 11:30:15 #መረጃ
የባልደራስ ፓርቲ መስራች አባልና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከባልደራስ በፍቃዳቸው ለመሰናበት በመልቀቂያ ደብዳቤ ሊጠይቁ መሆኑ ከፓርቲው የውስጥ ምንጮች መረጃዉ ተሰማ።

            ሚያዚያ 18/2015
                ኢትዮጵያ

"አማራነት በመቱት ቁጥር ይበልጥ ስሜቱ እየገባን መጥቷል ብለዋል።

አንጋፋው ፖለቲከኛ የባልደራስ ፓርቲ  ሥራ አስፈጻሚ አባልና የድ/ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በቅርብ ጊዜ ከእስር የተፈቱ ሲሆን  የፖለቲካ አቅጣጫ ለውጥ ለማድረግ ማሰባቸው ከፓርቲዉ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መረዳት ችለናል።

በአሁኑ ጊዜ በአማራ ሕዝብ የታወጀው ጦርነት አጥፍቶ የመጥፋት ቅስቀሳ የለየለት ውንብድና አማራን አጥፍቶ ሀገር ለመበትን መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው የሚሉት አቶ ስንታየሁ  አማራ በህልውና አደጋ የአዲስ አበባ ነዋሪ በጠቅላይነት ባርነት ውስጥ በወደቁበት ወቅት በምርጫ ጠባቂ  ቆሞ ቀር አጃቢ የቢሮ ፖለቲካ አሁን አይሰራም ሲሉ ሁሉም ሰዉ በህልውና ሕዝባዊ ትግል ብቻ ነው ነጻነቱን የሚያረጋግጠው በማለት የፖለቲካ መስመር የትግል ለውጥ ለማድረግ ከፓርቲዉ ሃላፊነት በፍቃዳቸው ለመልቀቅ መጠየቃቸው ተሰምቷል።

ከባለአደራው ጀምሮ ባልደራስ ፓርቲን በአዲስ አበባ ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር በማቋቋም ከምሥረታዉ ጀምረው የድርጅቱ የጀርባ አጥንት አምዕድ በመሆን ሲታገሉ የምናቃቸው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በተደጋጋሚ በኦህዴድ/ብልፅግና መንግስት በአማራነታቸው ሲንገላቱ መቆየታቸው ይታወቃል። ስልጣን ላይ ባለው የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በአዲስ አበባ ነዋሪ በተለይ በአማራ ሕዝብ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ከፍተኛ አደጋና መፈናቀል ቀድመው በመተንበይ በርካታ የማንቃት ስራዎችን ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር በመስራት ለነዋሪዉ ቢደክሙም የተረዳቸው ሕዝብ ባለመኖሩ ዛሬ የተደረሰበት ውጥንቅጥ የኦህዴድ ተረኛነት ፖለቲካ ነዋሪዎን ለከፋ ችግር እንደዳረገው በስፋት እየተገለፀ ይገኛል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ላለፋት  ለ22 አመታት በሰላማዊ ትግል ሲታገሉ መቆየታቸውና ከአስር አመታት በላይ በተደጋጋሚ በተለያዩ ቦታዎች መታሰራቸው ይገለጻል።
 
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
2.8K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ