Get Mystery Box with random crypto!

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ለመንግስት ሰራተኞች 45 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ አደረጉ የቱርክ ፕሬዚ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ለመንግስት ሰራተኞች 45 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ አደረጉ
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ለመንግስት ሰራተኞች 45 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የደመወዝ ጭማሪውን ያደረጉት በፈረንጆቹ የፊታችን ግንቦት 14 ቀን የሚካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

የደመወዝ ጭማሪው ዝቅተኛ ተከፋይ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ ወደ 15 ሺህ የቱርክ ሊሬ ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡

ቀጣዩን ምርጫ ቢያሸንፉም የተከሰተውን የዋጋ ንረት በመንግስት ሰራተኞች ላይ ጫና እንዳይፈጥር አስፈላጊ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

ባለፉት 20 ዓመታት ቱርክን የመሩት ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በስልጣን ዘመናቸው በሀገሪቱ ታላላቅ ለውጦች ማስመዝገባቸውን አር ቲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA