Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈጽሟል። በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት | ሰበር ዜና ET🇪🇹

ሳፋሪኮም 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈጽሟል።

በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት አልሚዎች የቴሌኮም መሠረተ ልማትን ከሀገር ውስጥ ኦፕሬተሮች የመከራየት አስገዳጅ አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል። ይኽም የኢትዮ ቴሌኮም የገበያ አቅምን ፈጥሯል። 

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ የግል የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዚሁ አስገዳጅ ሕግ መሠረት የራሱን የቴሌኮም መሠረተ ልማት መገንባት ስለማይችል የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት በኪራይ የመጠቀም ግዴታ ውስጥ ገብቷል።

በዚህም መሠረት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት መጠቀም የጀመረ ሲሆን፣ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥም ከኢትዮ ቴሌኮም ለሚያገኘው የመሠረተ ልማት መጋራት አገልግሎት 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ መፈፀሙን ሪፖርተር አስነብቧል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA