Get Mystery Box with random crypto!

መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ የሚመሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለተጓዦች ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ለመ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ የሚመሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለተጓዦች ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ለመክፈትና ለሰብአዊ እርዳታ የ24 ሰዓት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምቷል፡፡ ይህንኑ መሪው ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄምቲ ገልጸዋል፡፡ ሄሜቲ ከአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ እና ወዳጅ ካሏቸው አገራት ጋር ንግግር ከተደረገ በኃላ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡ ስለ ስምምነቱ እየተወራ ባለበት ወቅት በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሚገኘውን የወታደራዊ ዋና መስሪያ ቤት ለመቆጣጠር በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ አሁንም ድረስ እየተካሄደ ነው።
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA