Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ በጦርነቱ በካ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ
በጦርነቱ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መድረሱ ተገልጿል
ከተቀሰቀሰ አራተኛ ቀኑን በያዘዉ የሱዳን የከተማ ዉስጥ ጦርነት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና የአገሪቱ ጦር ዉግያ ዉስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ በሆነችዉ ሱዳን ኢትዮጵያዊንም ህይወታቸዉ እንዳለፈ ተሰምቷል።

በሱዳን 12 ዓመታትን የቆየዉና አስተያየቱን ለብስራት ራዲዮ የሰጠው የጤና ባለሙያ ወንድወሰን ጌትነት፤ ከትናንት በስቲያ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ኦምዱርማን በተሰኘዉ አካባቢ በጦርነቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን በጦር ጄት ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ተናግሯል። እስካሁን ከ10 በላይ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ ሞተዋል ያለም ሲሆን፤ በትናትናዉ ዕለት በካርቱም ( ጅሬፍ ) በደረሰ ሌላ ጥቃት፤ ባለትዳሮች ሕይወታቸውን ሲያጡ የሦሥት ዓመት ሕጻን ልጃቸዉ ከጥቃቱ መትረፉን ገልጿል።

በተጨማሪም በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይም ጥቃት መድረሱን የገለጸው ወንድወሰን፤ የትኞቹ ታጣቂዎች እንደፈጸሙት ባያረጋግጥም የኤምባሲዉን ቅጥር ግቢ ጥሰዉ በመግባት በግቢዉ በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባለቤት በሆነበት የመጠለያ ማዕከል ዉስጥ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ አጸያፊ ተግባራት ጭምር መፈጸማቸዉን ተናግሯል።

የኤምባሲዉ ጥበቃዎች በጦርነቱ ወቅት ከግዳጅ ቦታቸዉ በመነሳታቸዉ የተባለዉ ጥቃት መድረሱንና፤ ታጣቂዎቹ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ዘረፋዎችን መፈጸማቸዉንም ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን ልዩ ተወካይ ባወጣው መረጃ፤ በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት እስከ አሁን በትንሹ 200 ሰዎች መሞታቸው የገለጸ ሲሆን፤ 1 ሺሕ 8 መቶ ያህል ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸዉን አስታውቋል፡፡
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA