Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ያሉ የመንግስት ሰራተኞች፤ በአስር ቀናት ውስጥ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

በትግራይ ክልል ያሉ የመንግስት ሰራተኞች፤ በአስር ቀናት ውስጥ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ተላለፈ
በትግራይ ክልል መንግስት ስር ባሉ መዋቅሮች ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች፤ በአስር ቀናት ውስጥ በየመስሪያ ቤቶቻቸው ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ተላለፈ። በክልሉ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች፤ ውዝፍ የሶስት ወር ደመወዝ ክፍያ መሰጠት መጀመሩም ተገልጿል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የትግራይን ክልልን ተቆጣጥሮ የቆየው የመከላከያ ሰራዊት፤ የመቐለ ከተማን ለቅቆ ከወጣበት ከሰኔ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች መደበኛ ስራ አቁመው ቆይተዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሰብለ ካህሳይ፤ መደበኛ ስራ ተቋርጦ በቆየበት ጊዜ የክልሉ መንግስት ሰራተኞች በመስሪያ ቤቶቻቸው ይገኙ የነበረው ወጥ ባልሆነ ሁኔታ እንደነበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

“ፕሮግራም ወጥቶ ነበር ሰራተኛ ወደ ቢሮ ይገባ የነበረው። በሳምንት አንድ ቀንም [የሚገባ ነበር]። አንዳንድ ስራ የበዛበትም፤ ግማሽ ግማሽ ቀን ነው ስራ ይገባ የነበረው” ሲሉ ላለፉት አንድ ዓመት ከስምንት ወር ገደማ የነበረውን የስራ ሁኔታ አስረድተዋል። የፌደራል መንግስት እና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ በተፈራረሙት የሰላም ስምምነት መሰረት ባለፈው መጋቢት ወር አጋማሽ ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙን ተከትሎ፤ ሰራተኞችን በመደበኛ ሁኔታ ወደ ስራ የማስገባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ኮሚሽነሯ አስታውቀዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA