Get Mystery Box with random crypto!

“ከራያ አላማጣ ህዝብ ፍላጎት ውጪ የሚመጣ ማንም የህወሓት አመራር ወደ አላማጣ አይገባም”። ወደ ከ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

“ከራያ አላማጣ ህዝብ ፍላጎት ውጪ የሚመጣ ማንም የህወሓት አመራር ወደ አላማጣ አይገባም”። ወደ ከተማዋ ደፍረው ቢገቡም የሚጠብቃቸውን እርምጃ ያውቁታል ብለዋል።
ወያኔና የወያኔ ደጋፊ ወደ አካባቢያችን ቢመጣ ፍርድ የሚያገኘው ከራያ ወጣት እንጂ ከሌላ አካል አደለም።
ወያኔና የወያኔ ደጋፊ ጥይት ታጥቆ በር ተኽላይን አይሻገርም።
አሁን ያለው የግዚያዊ አስተዳደር መዋቅር የሚነሳው ህዝበ ውሳኔ የሚካሄድ ከሆነ በህዝበ ውሳኔ ወቅት ብቻ ነው።
አሁን ያለው ግዚያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት አውቆት ይሁንታ ሰጥቶትና በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት እንጂ በጉልበት እንዳልሆነ ሁሉም ልያውቀው ይገባል።
የወያኔ አመራር ዳግም አላማጣ የሚረግጠው የሰራውን ወንጀል አምኖ እጁን ለካቴና ለመስጠት እንጂ አከባቢውን ለመምራት አይመጣም ።
ወያኔ የሰላም ስምምነቱ ጥሶ ድጋሚ ጦርነት አነሳለሁ በር ተኽላይን እሻገራለሁ ካለ ጠቡ ከጀግናው ሀገር መከላከያ ጋር እንጂ የራያ ወጣት ጋር አይሆንም(አዩዘሀበሻ)።
-የአላማጣ ከተማ ከንቲባ እና የወሎ ራያ አማራ ወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሃይሉ አበራ
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA