Get Mystery Box with random crypto!

የተለያዩ አገራት ሱዳን የሚገኙ ዜጎቻቸው ደኅንነት እንዳሳሰባቸው በመግለጽ ላይ ናቸው። ኬንያ ግጭቱ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የተለያዩ አገራት ሱዳን የሚገኙ ዜጎቻቸው ደኅንነት እንዳሳሰባቸው በመግለጽ ላይ ናቸው። ኬንያ ግጭቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ ከተባባሰ 30 ሺህ ዜጎቿን ከአገሪቱ የሚያስወጣ ግብረ ኃይል ማቋቋሟን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ግብረ ኃይሉ እስከዚያው ለኬንያዊያኑ የአስቸኳይ ዕርዳታ አቅርቦትን እንደሚያስተባብር የገለጡት ዘገባዎቹ፣ እስካሁን ባለው መረጃ በግጭቱ የተገደለ ኬንያዊ እንደሌለ ጠቅሰዋል። ባሁኑ ወቅት የሱዳን የአየር ክልል ዝግ ሲሆን፣ የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያም የግጭት ቀጠና ኾኗል። በተመሳሳይ፣ የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደዔታ ምስጋኑ አረጋ በኢትዮጵያ ከሱዳን አምባሳደር ጋር ትናንት ባደረጉት ውይይት፣ በአገሪቱ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ደኅንነት እንዳነሱላቸው ሚንስቴሩ ገልጧል። አራተኛ ቀኑን በያዘው ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 እንዳለፈ መረጃዎች ያመለክታሉ።
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA