Get Mystery Box with random crypto!

አምነስቲ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአማራ ክልል በቅርቡ ከተቀሰቀሰው ሁከት ጋር በተያያዘ የታሠሩ ሰ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

አምነስቲ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአማራ ክልል በቅርቡ ከተቀሰቀሰው ሁከት ጋር በተያያዘ የታሠሩ ሰባት የመገናኛ ብዙኀን ሠራተኞችን ባስቸኳይ ከእስር እንዲለቁ አዲስ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። አምነስቲ፣ ባለሥልጣናቱ ባንዲት አንስት ጋዜጠኛ ላይ ተፈጸመ የተባለውን አካላዊ ጥቃትም እንዲያጣሩ ጠይቋል። መንግሥት "የኹሉንም ዜጎች ሃሳብን የመግለጽና ሰላማዊ ተቃውሞ የማድረግ መብት" እንዲያከብርም አምነስቲ ጥሪ አድርጓል። ድርጅቱ፣ በአማራ ክልል በቅርቡ የተደረጉ የተኩስ ልውውጦችና ሁለት ረድኤት ሠራተኞች በክልሉ ውስጥ መገደላቸውም እንዳሳሰበው ገልጧል(wazema)።
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA