Get Mystery Box with random crypto!

የተመድ ዋና ጸሀፊ ወደ ትግራይ ለመጓዝ ይዘውት የነበረው እቅድ፤ በኢትዮጵያ መንግስት “ውድቅ መደረ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የተመድ ዋና ጸሀፊ ወደ ትግራይ ለመጓዝ ይዘውት የነበረው እቅድ፤ በኢትዮጵያ መንግስት “ውድቅ መደረጉን” አንድ ምስጢራዊ ሰነድ አጋለጠ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፤ ወደ ትግራይ ለመጓዝ የያዙት እቅድ በኢትዮጵያ መንግስት ውድቅ በመደረጉ “ክፉኛ ተበሳጭተው” እንደነበር “ዋሽንግተን ፖስት” ጋዜጣ የተመለከተው አንድ ምስጢራዊ ሰነድ አጋለጠ። የዋና ጸሀፊው ጥያቄ በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት አለማግኘቱን በመግለጽ ለጉተሬዝ ደብዳቤ የጻፉላቸው፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መሆናቸው በዚሁ ምስጢራዊ ሰነድ ይፋ ተደርጓል።

ጉተሬዝ የትግራይ ጉብኝታቸው መሰረዙን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የነበሯቸውን መስተጋብሮች የያዙት ምስጢራዊ ሰነዶች አፈትልከው የወጡት ከአሜሪካ መንግስት እጅ ነው። “ዲስኮርድ” በተሰኘው የመልዕክት መለዋወጫ “ሰርቨር” የተለቀቁትን እነዚህን ሰነዶች ያወጣው፤ የማሳቹሴትስ የአየር ኃይል ብሔራዊ ዘብ ባልደረባ የነበረ የ21 ዓመት ወጣት ነው።

አሜሪካ “በወዳጆቿ እና አጋሮቿ ላይ ስታካሄድ የቆየችውን ስለላ ያጋለጡ ናቸው” ከተባለላቸው ሰነዶች መካከል አራቱ፤ ከጉተሬዝ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን “ዋሽንግተን ፖስት” ትላንት ሰኞ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል። የካቲት 10፤ 2015 የተጠናቀረ አንድ ሪፖርትን በማሳያነት የጠቀሰው ዘገባው፤ ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያደርጉት ያቀዱት ጉዞ መሰረዙን በተመለከተ፤ በወቅቱ በተመድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ታዬ ታዬ አጽቀስላሴን ለመጋፈጥ ፈልገው እንደነበር አትቷል።

ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያቀኑ አቅደው የነበረው፤ በክልሉ የነበረውን ጦርነት ላስቆመው የሰላም ስምምነት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ነበር ተብሏል። ንደ “ዋሽንግተን ፖስት” ዘገባ ከሆነ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ እቅድ የተጨናገፈው፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጉብኝቱን ውድቅ የሚያደርግ ደብዳቤ ከላኩላቸው በኋላ ነው(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)።
ሚያዝያ 11/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA