Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠየቀ የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታችሁ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠየቀ
የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታችሁ ወጥታችሁ ላመለጣችሁ የከተማችንና አካባቢው ሙስሊሞች በሙሉ!!
ዛሬ በነበረው የኢድ ሰላት ፕሮግራም ላይ ለመታደም ጥሪያችንን አክብራችሁ በአንድነት  አምራችሁና ደምቃችሁ ግዙፉ የከተማችን ውበት ሆናችሁ በመዋላችሁ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በድጋሚ እንኳን ለ1444 ዓ.ሂ  የኢድ አልፊጥር በዓል  በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዛሬው እለት የተሰገደው የኢድ ሰላት በሰላም፣በደስታ መጠናቀቁ ቢያስደስትም የዒድ ሰላት ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት ከነበረው ሰአት ቀድሞ በመሰገዱ የዒድ ሰላት ላመለጣችሁ የከተማችን ሙስሊሞች ይቅርታ እንጠይቃለን።

በትናንትናው እለት ከፌደራል መጅሊስ ጋር በጋራ በሰጠነው መግለጫ ሸሪአውን በጠበቀ መልኩ በእለቱ ንግግሮች እንደማይኖሩና በማለዳ ሰግደን እንደምንበተን ለህዝባችን ገልፀን ቢሆንም በእለቱ የተገኙት ሚድያዎች በአብዛኛው በሚባል መልኩ ትኩረት ሰጥተው ባለማስተላለፈቸው እና ከሚዲያዎቹ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በሰፊው  ባለመጠቀማችን ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ተረድተናል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት የነበረውን ሂደትን ለማሻሻል በሚል መልካም እሳቤ በተፈጠረ ክፍተት ሰላት ላመለጣችሁ ሁሉ ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ የሚስተካከል መሆኑን ህዝባችን እንዲገነዘብ እያልን፣
በበጎና ገንቢ በሆነ መልኩ አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የከተማችን ነዋሪዎች ምስጋና እያቀረብን በዓሉ የሰላም የደስታ፣የመተዛዘን፣የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን።
@ET_SEBER_ZENA