Get Mystery Box with random crypto!

በአርሲ ዞን በድጋሚ ለቅርጫ ከተገዛ ሰንጋ ውስጥ 7.5 ግራም ወርቅ ተገኘ በምስራቅ አርሲ ለትንሳ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

በአርሲ ዞን በድጋሚ ለቅርጫ ከተገዛ ሰንጋ ውስጥ 7.5 ግራም ወርቅ ተገኘ

በምስራቅ አርሲ ለትንሳኤ በዓል የገዙት በሬ ለእርድ በሚቀርበበት ሰዓት በሀሞቱ ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ መገኘቱን የጢዮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ግረማ ጣፋ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቦቹ  ኩማ ተሰማ እና ንጉሴ ዲንቃ የተባሉ ሲሆን ለበዓል ቅርጫ በ38ሺህ ብር በሬ ገዝተው  በሚያርዱበት ወቅት  በበሬው ሃሙት ውስጥ 7.5 ኪሎግራም የሚመዝን ወርቅ አግኝተዋል። ወርቁ  ሃያ አንድ ሺ አምስት መቶ ብር መሸጡ ተሰምቷል።

ከቀናት በፊትም በዚሁ አካባቢ 18.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ በበሬ ሀሞት ላይ ስለመገኘቱ እና ወርቁን 53ሺብር ስለመሸጡ ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው እንዳሁኑ ይፋ የወጣ ነገር ባይኖርም በተደጋጋሚ  በበሬዎች ሃሞት ላይ ወርቅ ስለመገኘቱም ኮማንደር ግርማ ጣፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Via: ዳጉ ጆርናል
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA