Get Mystery Box with random crypto!

አጫጭር መረጃዎች በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የሱዳን የባህር ሃይል ጦር አዛዥ የነበሩት ፋት | ሰበር ዜና ET🇪🇹

አጫጭር መረጃዎች በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ

የሱዳን የባህር ሃይል ጦር አዛዥ የነበሩት ፋት አል ራህማን ሙህይዲን ለአልጀዚራ እንደተናገሩት “ካርቱም በሙሉ” በጦር ኃይሉ ቁጥጥር ስር መግባቷን ገልፀዋል። "ለሱዳን ህዝብ እንደማረጋግጠው ከሁለት ግዛቶች በስተቀር ሁሉም ግዛቶች በጦር ኃይሉ ቁጥጥር ስር ናቸው" ሲሉ አክለዋል።

ከ20,000 በላይ የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች ለሠራዊቱ እጃቸውን መስጠታቸው የሱዳን የባህር ሃይል ጦር አዛዥ የነበሩት ፋት አል ራህማን ሙህይዲን  ተናግረዋል።አንዳንዶች ግን እስከ ሞት ድረስ መታገል ይፈልጋሉ” ሲል ሙህይዲን አክለዋል። አስተያየታቸውን ግን በገለልተኛነት አካል ማረጋገጥ አልተቻለም።

በካርቱም የፖለቲካ ተንታኝ አሽራፍ አብደል አዚዝ የግጭቱ ምንጮች በጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን እና በአርኤስኤፍ መሪ ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን “ሄሜቲ” ዳጋሎ መካከል “ግላዊ” ፀብ ናቸው ብለዋል። "ነገር ግን መጥፎው የሰብአዊ ሁኔታ ግጭቱን እንዲያቆሙ በሁለቱም ወገኖች ላይ ጫና ያሳድራል" ሲሉ ከካርቱም ተናግረዋል።

ድንበር የለሹ የሀኪሞች ቡድን ባልደረባ ባክሪ ባሽር ለአልጀዚራ እንደተናገሩት በሱዳን ያለው የጤና ሁኔታ “ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ” መልኩ አስጊ መሆኑን ተናግረዋል። ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ባሽር እንደተናገሩት “ጦርነቱ በዚህ ፍጥነት የሚቀጥል ከሆነ በሀገሪቱ ያለውን የጤና ስርዓት ሙሉ በሙሉ እናጣለን የሚል ስጋት ተጋርጦብናል” ብለዋል።

በካርቱም ከሚገኙት 59 ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች 39ኙ ህሙማንን ማገልገል የማይችሉ መሆናቸውን የሱዳን የህክምና ኮሚቴ አስታውቋል።በመግለጫውይ አንዳንድ ሆስፒታሎች በቦምብ መመታታቸውን ገልጿል። ታካሚዎችን እና የህክምና ባለሙያዎችን ለመጠበቅ “አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት” እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

በጦር ሠራዊቱ እና በፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ቢያንስ 270 ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የሱዳንን የጤና  ሚኒስቴርን ጠቅሶ አስታውቋል። ሌሎች 2,600 ሰዎችም ቆስለዋል ሲል አክሏል።
ዳጉ_ጆርናል

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA