Get Mystery Box with random crypto!

የጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤቶች ሊከሰሱ ነዉ ተባለ ከአንድ አመት ከስድስ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤቶች ሊከሰሱ ነዉ ተባለ

ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት በኬኒያ የታገተው የአቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል  ቤተሰቦች በሁለቱ ተቋማት ላይ ክስ ሊመሰርቱ እንደሆነ አስታዉቀዋል፡፡

በሳምሶን ጉዳይ  የውጭ ጉዳይ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ነው ያሉት ቤተሰቦቹ፤ ክስ ሊመሰሩት መሆኑ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሃለፎም እስካሁን በመስራቤቶቹ በኩል እየተሰጠን ያለው መረጃ ለዜጋ የሚመጥን አይደለም ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተሰጠን ምላሽ እና አሁንም እየተሰጠን ያለው ተመሳሳይ ነው ብለዋል፡፡

በኬኒያ የሚገኝው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግለሰቡ ዙርያ ምርመራ እያካሄድን ነው ከማለት ውጭ የሚሰጠን ተስፋ የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፌደራል እንደዚሁም በኦሮሚያ ክልል ማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ዳባ ጩፋ የአቶ ሰምሶን ጉዳይ እልባት አለማግኝት በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድክመት ነው ብለዋል፡፡

ኤምባሲው ልክ እንደ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ ሲጠበቅበት ነገሩን በቸልታ እያለፈው ይገኛል ብለዋል፡፡

የአቶ ሳምሶን ቤተሰቦች ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ቢያቀርቡም አንድም ውጤት አለማምጣቱትን ነው የገለጹት፡፡

በመሆኑም የአቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል   ቤተሰቦች በሁለቱ ፅሕፈት ቤቶች ላይ ክስ በመክፈት የልጃቸዉን አድርሻ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡                      
(ሄኖክ ወልደ ገብርኤል)
ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA