Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ ከተኮሰ በኋላ አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል ማዘጋጀቷን ገለጸች ሩሲያ ከተኮሰ በኋላ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

ሩሲያ ከተኮሰ በኋላ አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል ማዘጋጀቷን ገለጸች

ሩሲያ ከተኮሰ በኋላ አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል ማዘጋጀቷን ገለጸች።

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 15ኛ ወሩ ላይ ሲሆን ጦርነቱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም እሚቀጥል ይመስላል።

አሜሪካ እና ሌሎች የዓለማችን ሀገራት ለዩክሬን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በመርዳት ላይ ናቸው።

ሩሲያ በበኩሏ ለዩክሬን የሚደረጉ የጦር መሳሪያ ድጋፎች ልዩነት እንደማይፈጥሩ ከዚህ በፊት አስታውቃለች።

ይህ በዚህ እንዳለ በየጊዜው አዳዲስ እና ከዚህ በፊት የተፈበረኩ የጦር መሳሪያዎችን በማዘመን ላይ ትገኛለች።

አሁን ደግሞ ቶርናዶ ኤስ የተሰኘ በየደቂቃው አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል መስራቷን ገልጻለች።

እንደ አርቲ ዘገባ ይህ የጦር መሳሪያ አንድ ጊዜ በሚያደርሰው ጥቃት ብቻ ከ12 ስታዲየም በላይ ስፋት ላይ ያለን ስፍራ ማውደም ይችላል AlAin።
ሚያዝያ 11/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA