Get Mystery Box with random crypto!

“የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ”- ጄነራል ዳጋሎ ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

“የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ”- ጄነራል ዳጋሎ

ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋና አዛዥ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ” አሉ።

ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ “አሁን ላይ እየተዋጋን ያለነው ከሱዳን ጦር ጋር ሳይሆን ከቅጥረኛ ኃይሎች ጋር ነው፤ ምክንያቱም 90 በመቶ የሱዳን ጦር ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ብለዋል።

ዳጋሎ አክለውም፤ “ከዚህ በኋላ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዣ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተቀምጦ መነጋገር ምንም ዋጋ እንደሌለውና አልቡርሃን ከዚህ በኋላ ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ጦርነት አልፈልግም ነበር፣ ከጦርነት ይልቅ ሰላም እና መረጋጋትን ነው የምመርጠው” ያሉት ዳጋሎ፤ “ወደ ጦርነት እንድንገባ የገፋፋን አልቡርሃን ነው፤ አሁን ግን እጁ ላይ ምንም አልቀረለትም” ሲሉም ተናግረዋል Alain።
@ET_SEBER_ZENA