Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የ72 ሰዓት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የ72 ሰዓት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለ72 ሰዓት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አስታወቁ።

በተቀናቃኝ ጎራ ተሰልፈው እየተፋለሙ ያሉት የሱዳን ጦርና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ሰኞ እኩለ ሌሊት እንደተጀመረ ተገልጿል።

በሱዳን ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ የአሁኑን ጨምሮ ቢያንስ ለሦስት ጊዜ ያህል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር ፤ እስካሁን የነበሩት የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተፋርሰው ውጊያው ቀጥሎም ቆይቷል።

በመደበኛው ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ለ48 ሰዓታት ያህል ድርድር ከተደረገ በኋላም የአሁነኛው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን ብሊንከን ገልጸዋል።

ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በተናጠል አስታውቀዋል።

ጦርነቱ ሚያዝያ 7/ 2015 ዓ.ም ከተቀሰቀሰበት እለት ጀምሮ ቢያንስ ከ400 በላይ ዜጎች ሕይወት መቀጠፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA