Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-03-31 17:55:21
በህገ-ወጥ መንገድ የተገጠሙ ቆጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ ጎሮ አካባቢ ልዩ ስሙ አሳማ እርባታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አስራ ሰባት ቆጣሪዎች በህገ-ወጥ መንገድ ተገጥመው ተገኝተዋል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ ተገጥመው የተገኙት ቆጣሪዎች ከነፍጆታቸው አጠቃላይ ግምት ከሶስት መቶ አርባ ሶስት ሺ ብር በላይ ነው፡፡

የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ህግ ክፍል ከፖሊስ ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መንገድ የተገጠሙትን ቆጣሪዎች፣ኬብልና ምሰሶ ተነስቶ ወደ ተቋሙ ገቢ እንዲሆን አድርጓል፡፡

የአካባቢው ፖሊስ ህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ ምርመራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
835 viewsedited  14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 11:57:31
አገልግሎቱ የ10 ከተሞች የዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሊያከናውን ነው
*****************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ10 ከተሞች የዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ የማሻሻያ ፕሮጀክት ስራ ሊያከናውን ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በነቀምት፣ አምቦ፣ አሶሳ፣ ቢሾፍቱ፣ ደብረብርሃን፣ ሱሉልታ፣ ጅጅጋ፣ ሆሳዕና፣ አሰላ እና ዲላ ከተሞች በሶስት ሎት ተከፍሎ የሚከናወን ይሆናል፡፡

በፕሮጀክቱ 1278 የመካከለኛ መስመር (15ኬ.ቪ) ማሻሻያ ግንባታና ነባር መስመሮችን የማንሳት እና 2168 ነባር የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ማሻሻያ ሥራ ይከናወናል፡፡

ስራው የሚከናወነው ከዓለም ባንክ በተገኘ 47 ሚሊየን 500 ዶላር የፋይናንስ ምንጭ እና 17 ሚሊየን 892 ሺህ 740 ብር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተመደበ በጀት ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በማሰራጫ መስመሮች ላይ የሚታየውን የኃይል መቆራረጥ፤ መዋዠቅንና ኃይል ማነስን በማሻሻል በከተሞቹ እያደገ የመጣውን የደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት በመጠንና በጥራት ለሟሟላት ያስችላል፡፡

በተጨማሪም አዳዲስ ደንበኞችን ማገናኘት የሚያስችል የኔትዎርክ አቅምን ይፈጥራል፣ የዲስትሪቢዩሽን የቴክኒካል ኃይል ብክነትን ይቀንሳል፣ በከተሞቹ በ100 ኪሎ ሜትር በመካከለኛ መስመሮች ላይ የሚታየውን አማካይ የመቆራረጥ ድግግሞሽ 45 በመቶ እንዲሁም በ100 ኪ.ሜ አማካይ የማቋረጥ ቆይታ 50 በመቶ ይቀንሳል፡፡

ፕሮጀክቱ በተያዘው በጀት አመት ተጀምሮ በ2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.1K viewsedited  08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 15:35:36
ክቡራን ደንበኞቻችን በሃይል መጨናነቅ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን #የሃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር ለመቀነስ የሃይል ጭነት በማይበዛባቸው ስዓት ማለትም ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ስዓት በመጠቀም ሊፈጠር የሚችለውን የሃይል መቆራረጥና ይቀንሱ!! ከዚህ በተጨማሪም ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎንም በቴሌ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግና በሲ.ኢ.ቢ ብር በመክፈል ጊዜዎትንና ገንዘብዎን ይቆጥቡ!!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.4K viewsedited  12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 11:03:49
በአካል፣ በንበረትና በህይወት ላይ ሊደርስ የሚችለውን #የኤሌክትሪክ አደጋ እንዴት መከላከል እንችላለ?

ኤሌክትሪክ አስፈላጊ የመሆኑን ያክል በአጠቃቀም ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረገ ህይወትን ወይም ንብረትን በቅፅበት ሊያሳጣ ይችላል፡፡ ከዚህ በታቸ የተዘረዘሩት ለኤሌክትሪክ አደጋ መከሰት ምክንያት ስለሚሆኑ መሰል ተግባራትን ከማከናወን መቆጠብ ያስፍልጋል፡፡

• በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች አቅራቢያ ልጆች ጨዋታ እንዲጫወቱ ከመፍቀድ፣
• በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች አቅራቢያ በጣም ተጠግቶ የንግድ ሥራዎች ከማከናወን፣
• በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች በዕርጥብ ጨርቅ ወይም በእንጨት ከመነካካት፣
• ያልተሸፈነ መስመር በብረት ወይም በእርጥብ እንጨት መነካካትና ከማገናኘት፣
• እሳት ሲፈጠር ለሚመለከተዉ አካል በአፋጣኝ ከማሳወቅ ይልቅ በእንጨት፣ በውሀ፣ በአፈር በብረት ወዘተ…..ለማጥፋት ከመሞከር፣
•የኤሌክትሪክ መስመር ሲበጠስ፣ ምሰሶ ሲወድቅ ወዲያዉኑ ለሚመለከተው አካል ከማሳወቅ ይልቅ በእንጨት፣ በብረት ለማንሳት መሞከር ለአደጋ ይዳርጋል፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ይህንን ተገንዝበን መሰል ተግባራትን ከማከናወን እንድንቆጠብና ራሳችን እንዲሁም በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ ከአደጋ ልንጠብቅ ይገባል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.9K viewsedited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 12:09:20
ከ57 ሚሊየን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሊከናወን ነው

በአዲስ አበባ ከተማ 4ኛ ምዕራፍ የዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሊከናወን መሆኑን የዲስትሪቢዩሽን ሪሀብልቴሽን ፕሮግራም ኃላፊ አቶ ጎሳየ ተ/ወልደ ገለፁ፡፡

እንደ ኃላፊው ገለፃ በአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን እድገትን ተከትሎ የኃይል ፍላጎት ከመቼዉም ጊዜ በላይ የጨመረ ከመሆኑ በተጨማሪ እድገቱን መሸከም የሚችል የዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ አብሮ ባለማደጉ ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ፤ የኃይል ማነስ እና የኃይል ብክነት በመከሰቱ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድር ችሏል ብለዋል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ምስፈንጠሪየውን ይጫኑ http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/news/detail/494
3.6K viewsedited  09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 10:12:15
ውድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን፤ የተጠቀማችሁበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ቀላልና ምቹ በሆነው #የቴሌ_ብር መተግበሪያ ይክፈሉ፡፡ *127# አጭር ቁጥር በመጠቀም ብቻ ሳይጉላሉና ሳይንገላቱ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ካሉበት ሆነው በቀላሉ ይክፈሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.7K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 13:08:54
ለአቅም ማሻሻያ ስራ ሲባል የሚቋረጥ የሃይል አቅርቦት

በባሌ ዞን በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት አየጨመረ በመምጣቱ ከሮቤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በሚወጡ ኃይል ማሰራጫ መስመሮች ላይ የኃይል መጨናነቅ ችግር አስከትሏል፤ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የሚወጡ መስመሮችን አቅም ማሻሻያ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

ስለሆነም ችግሩ እስኪፈታ ድረስ በሮቤ፣ ጎባ፣ ሲናና፣ አጋርፋ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው እንዲሁም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲና አካባቢው የምትገኙ ደንበኞቻችን የኃይል አቅርቦቱን በፈረቃ ለመስጠት የተገደድን መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.2K viewsedited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 11:49:11
ከ12 ሺ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ በመከናወን ላይ ነው

ከ12 ሺ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ መደበኛ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ በመከናወን ላይ ነው፡፡

ግንባታው በመከናውን ላይ የሚገኘው በአምስት የ40/60 ኮንዶሚኒየም ሳይቶች ሲሆን በቦሌ አያት 2፣ በቦሌ አያት 4፣ ቱሪስት፣ ኢምፔሪያል እና መሪ ሎቄ ሳይቶች የሚካሄደው የዚህ ግንባታ አፈፃፀም በአማካኝ ከ42.5 እስከ 73.61 በመቶ ደርሷል፡፡

ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 12 ሺ ሁለት መቶ ሀያ አምስት ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህ ግንባታ 10.52 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመርና 4.58 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ግንባታ እንዲሁም የቆጣሪ ልጠፋ ስራ እየተካሄደ ሲሆን የመካከለኛ መስመር ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

በተጨማሪም በቦሌ አያት 2፣ ኢምፔሪያል፣ መሪ ሎቄ፣ በቦሌ አያት 4 እና ቱሪስት ሳይቶች በዕቅድ እንዲተከሉ ከተያዙት ትራንስፎርመሮች መካከል ቢያንስ 60ቹ ተተክለዋል፡፡ እስካሁን በተከናወነው ግንባታ ከቦሌ አያት ሳይት 27 ብሎኮች እንዲሁም ከመሪ ሎቄ ሳይት ደግሞ 12 ብሎኮች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

የቦሌ አያት 2፣ቱሪስትና መሪ ሎቄ ሳይቶች በመከናወን ላይ የሚገኘው ግንባታ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እየተሰራ ሲሆን የቀሪዎቹ መሪ ሎቄ እና ቦሌ አያት 4 ሳይቶች ግንባታ ደግሞ ሚያዝያ 30 እና ግንቦት 30፤2015 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.2K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 15:17:24
ለጥገና ሥራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት /በአዲስ አበባ/

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የጥገና ስራ የሚያከናውን በመሆኑ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ቦታዎች የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ ይሆናል፡፡

የሚቋረጥበት ቀን :-እሁድ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 3፡00 ድረስ፡- በኖህ አደባባይ፣ በካፒታል ሲሚንቶ፣ በአይካ አዲስ፣ በጆሞ 3 በከፊል፣ በፋና፣ በአየር ጤና፣ በናትራን፣ በለማ ነጎ ሰፈር፣ በአየር ጤና ሞቢል ጋዝ እና አካባቢው፣

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ድረስ፡- በቻይና ቱቦ፣ በቆሼ፣ በረጲ መድሐኒዓለም ቤ/ክ፣ በፋና ሬዲዮ፣ በስልጤ ሰፈር መውጫ፣ በፋኑኤል ቤ/ክ፣ በአጀንባ ኮንደሚኒየም፣ በዋልያ ብረታ ብረት፣ በዓለም ገና ኢንዱስትሪ መንደር፣ በፉሪ ሬዲዮ ጣብያ፣ በሃጂ ሪል እስቴት፣ በወርዶፋሎጅ፣ በዳርፉር ሰፈር፣ በጆሞ 2 እና አካባቢው፣

እንዲሁም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ፡- በአየር ጤና ሳሚ ካፌ፣ በታቦት ማደርያ፣ በመሀንዲስ ሰፈር፣ በቴሌ፣ በሰላ ከብት እርባታ፣ በወለቴ ኢንዱስትሪ መንደር፣ በካራ ቆሬ ት/ቤት፣ በወሎ ኮንደሚኒየም መውጫ፣ በወለቴ ቶታል ኖክ ድረስ፣ በካራ መድሐኒያለም መውጫ፣ በኢንዱስትሪ መንደር፣ በአየር ጤና ት/ቤት፣ በአየር ጤና መስጊድ፣ በኪዳነ ምህረት ቤ/ክ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ ይሆናል፣

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.2K viewsedited  12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 12:07:55
ውድ ደንበኞቻችን #እናስታውስዎ

ነገ #ቅዳሜ_መጋቢት_16 ቀን 2015 ዓ.ም ዋናው መስሪያ ቤትን ጨምሮ የክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤቶች፣ ዲሰትሪክቶች እና በየደረጃው የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/@EthiopianElectricUtility
ድረገፅ: http://www.eeu.gov.et
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/EEUOfficial
1.5K viewsedited  09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ