Get Mystery Box with random crypto!

ከ12 ሺ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግ | Ethiopian Electric Utility

ከ12 ሺ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ በመከናወን ላይ ነው

ከ12 ሺ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ መደበኛ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ በመከናወን ላይ ነው፡፡

ግንባታው በመከናውን ላይ የሚገኘው በአምስት የ40/60 ኮንዶሚኒየም ሳይቶች ሲሆን በቦሌ አያት 2፣ በቦሌ አያት 4፣ ቱሪስት፣ ኢምፔሪያል እና መሪ ሎቄ ሳይቶች የሚካሄደው የዚህ ግንባታ አፈፃፀም በአማካኝ ከ42.5 እስከ 73.61 በመቶ ደርሷል፡፡

ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 12 ሺ ሁለት መቶ ሀያ አምስት ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህ ግንባታ 10.52 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመርና 4.58 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ግንባታ እንዲሁም የቆጣሪ ልጠፋ ስራ እየተካሄደ ሲሆን የመካከለኛ መስመር ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

በተጨማሪም በቦሌ አያት 2፣ ኢምፔሪያል፣ መሪ ሎቄ፣ በቦሌ አያት 4 እና ቱሪስት ሳይቶች በዕቅድ እንዲተከሉ ከተያዙት ትራንስፎርመሮች መካከል ቢያንስ 60ቹ ተተክለዋል፡፡ እስካሁን በተከናወነው ግንባታ ከቦሌ አያት ሳይት 27 ብሎኮች እንዲሁም ከመሪ ሎቄ ሳይት ደግሞ 12 ብሎኮች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

የቦሌ አያት 2፣ቱሪስትና መሪ ሎቄ ሳይቶች በመከናወን ላይ የሚገኘው ግንባታ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እየተሰራ ሲሆን የቀሪዎቹ መሪ ሎቄ እና ቦሌ አያት 4 ሳይቶች ግንባታ ደግሞ ሚያዝያ 30 እና ግንቦት 30፤2015 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et