Get Mystery Box with random crypto!

ለአቅም ማሻሻያ ስራ ሲባል የሚቋረጥ የሃይል አቅርቦት በባሌ ዞን በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የኤሌክ | Ethiopian Electric Utility

ለአቅም ማሻሻያ ስራ ሲባል የሚቋረጥ የሃይል አቅርቦት

በባሌ ዞን በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት አየጨመረ በመምጣቱ ከሮቤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በሚወጡ ኃይል ማሰራጫ መስመሮች ላይ የኃይል መጨናነቅ ችግር አስከትሏል፤ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የሚወጡ መስመሮችን አቅም ማሻሻያ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

ስለሆነም ችግሩ እስኪፈታ ድረስ በሮቤ፣ ጎባ፣ ሲናና፣ አጋርፋ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው እንዲሁም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲና አካባቢው የምትገኙ ደንበኞቻችን የኃይል አቅርቦቱን በፈረቃ ለመስጠት የተገደድን መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et