Get Mystery Box with random crypto!

ለጥገና ሥራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት /በአዲስ አበባ/ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማከ | Ethiopian Electric Utility

ለጥገና ሥራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት /በአዲስ አበባ/

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የጥገና ስራ የሚያከናውን በመሆኑ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ቦታዎች የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ ይሆናል፡፡

የሚቋረጥበት ቀን :-እሁድ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 3፡00 ድረስ፡- በኖህ አደባባይ፣ በካፒታል ሲሚንቶ፣ በአይካ አዲስ፣ በጆሞ 3 በከፊል፣ በፋና፣ በአየር ጤና፣ በናትራን፣ በለማ ነጎ ሰፈር፣ በአየር ጤና ሞቢል ጋዝ እና አካባቢው፣

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ድረስ፡- በቻይና ቱቦ፣ በቆሼ፣ በረጲ መድሐኒዓለም ቤ/ክ፣ በፋና ሬዲዮ፣ በስልጤ ሰፈር መውጫ፣ በፋኑኤል ቤ/ክ፣ በአጀንባ ኮንደሚኒየም፣ በዋልያ ብረታ ብረት፣ በዓለም ገና ኢንዱስትሪ መንደር፣ በፉሪ ሬዲዮ ጣብያ፣ በሃጂ ሪል እስቴት፣ በወርዶፋሎጅ፣ በዳርፉር ሰፈር፣ በጆሞ 2 እና አካባቢው፣

እንዲሁም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ፡- በአየር ጤና ሳሚ ካፌ፣ በታቦት ማደርያ፣ በመሀንዲስ ሰፈር፣ በቴሌ፣ በሰላ ከብት እርባታ፣ በወለቴ ኢንዱስትሪ መንደር፣ በካራ ቆሬ ት/ቤት፣ በወሎ ኮንደሚኒየም መውጫ፣ በወለቴ ቶታል ኖክ ድረስ፣ በካራ መድሐኒያለም መውጫ፣ በኢንዱስትሪ መንደር፣ በአየር ጤና ት/ቤት፣ በአየር ጤና መስጊድ፣ በኪዳነ ምህረት ቤ/ክ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ ይሆናል፣

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et