Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-29 16:08:39
በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

በጋምቤላ ከተማ ንፋስ ቀላቀቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከጋምቤላ ተነስቶ ለደምብዶሎ ኃይል ማሰረጫ ኃይል የሚሰጥ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ፡- ደምብዶሎ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ቄሌም ወለጋ ዞን ስር የሚገኙ ቦታዎች ደምቢዶሎ፣ ሙጊ፣ ሀዋ ገላን፣ መቻራ፣ ጫንቃ፣ ቃቄ፣ ቄቤ፣ ጅማ ሆሮ ከተሞችና በአካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱ ቦታዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን አገልግሎቱን ወደ ቦታው ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አውቃችሁ፤ የጥገና ስራው ተጠናቆ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ እስከሚመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
5.3K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 14:00:08
የስቱዲዮ ፓናል ውይይት ፕሮግራም ጥቆማ

የተቋማችን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተቋሙ አጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ያደረጉት የስቱዲዮ ፓናል ውይይት ዛሬ ምሽት ከ2፡00 ዜና በኋላ በዋልታ ቴሌቭዥን ይተላለፋል፡፡

ስለሆነም በዚህ ውይይት ደንበኞች ሊያውቋቸው የሚገቡ ጉዳዮችና ተያያዥ መረጃዎች የሚዳሰሱበት ስለሆነ ውይይቱን እንዲከታተሉት በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
5.2K viewsedited  11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 11:11:24
ውድ የድህረ ክፍያ ደንበኞቻችን፤ የተጠቀማችሁበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በተዘረጉ የክፍያ አማራጮች በመጠቀም ይፈፅሙ፡፡ #ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ሲጠቀሙ አስፈላጊ ካልሆነ ወጪና እንግልት ያድናል! ኑሮንም ያቃልላል! በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመምጣት ጊዜዎትን፣ ጉልበትዎትንና ገንዘብዎትን አያባክኑ፡፡ ካሉበት ሆነው በተዘረጉ ቀላልና ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ብቻ ይጠቀሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
5.4K views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 15:00:56
ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን በሙሉ እንኳን 1444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
5.6K viewsedited  12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 14:59:50

4.9K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 11:58:21
አንድ ሺ 609 የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ

በአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በደብረ ብርሀን ዲስትሪክት ማስተባበሪያ ቢሮ ስር የሚገኙ አንድ ሺ 609 የአምስት የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

የደብረ ብርሀን ማስተባበሪያ ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ስምንት የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ አቅዶ 5 ቀበሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ካለፈው ዓመት ያልተጠናቀቁ 11 ቀበሌዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 16 ቀበሌዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

አገልግሎቱን ተደራሽ ለማደፍረግ 208 ነጥብ 69 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመርና 103 ነጥብ 26 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ ሲሆን 31 የተለያየ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች የተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡

ያልተጠናቀቁ የሶስት ቀበሌዎች ግንባታን በቅርቡ በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

የግንባታ ስራው በሚከናወንበት ወቅት መሰረተ ልማቱን ከስርቆት በመጠበቅ ረገድ የአካባቢው ህብረተሰብ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ማስተባበሪያ ቢሮው ገልፆ በቀጣይም ይህንን በጎ ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲል አሳስቧል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
4.8K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 13:45:52
በጣና በለስና አካባቢው የምትገኙ ደንበኞቻችን ከጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የጣና በለስ 132 ኪሎ ቮልት የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፓወር ትራንስፎርምር በመበላሸቱ በአካባቢው የሃይል አቅርቦቱ ተስተጓጉሏል፡፡

ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታት ከዳንግላ 66 ኪሎ ቮልት የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ካለው ርቀትና የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ካለው የአቅም ውስንነት ምክንያት የተፈለገውን ያህል አገልግሎት መስጠት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን ችግሩ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በኩል እስኪፈታ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
798 viewsedited  10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 12:33:38
ኤሌክትሪክ አስፈላጊ የመሆኑን ያክል በአጠቃቀም ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረግን በአካል፣ በንበረትና በህይወት ላይ ከፍተኛ የሆነ #አደጋ ሊያስክትል ይችላል፡፡ ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ሊደርስ የሚችለውን የኤሌክትሪክ አደጋ እንከላከል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
1.3K viewsedited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 15:03:21
ውድ ደንበኞቻችን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባችሁን በዲጅታል የክፍያ አማራጮች ለመፈፀምና ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የተያያዙ መረጃዎች በእጅ ስልኮቻችሁ እንዲደርሳችሁ ስልክ ቁጥሮቻችሁን በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕክል እንድታስመዘግቡ እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.5K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:26:07

4.1K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ