Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-17 10:13:59
በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ላይ በተፈፀመ ውደመት የሃይል አቅርቦት ተቋርጧል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከቦንጋ የኤሌክትሪክ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ /ሰብስቴሽን/ በመነሳት ለጠሎ ወረዳ እና አጎራባች አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው 33Kv ከፍተኛ መስመር ተሸካሚ መስመር በህገ ወጦቹ በመውደሙ አካባቢው ለጨለማ ተዳርጓል።

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን በተከሰተው ችግር ምክንያት ለተቋረጠው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቅርታ እየጠየቅን ስራው ተሰርቶ ወደነበረበት እስከሚመለስ ድረስ አማራጭ የኃይል ምንጮችን በመጠቀም በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን።

ከዚህ በተጨማሪ ወረዳው ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ስርቆት የሚፈፀምበት በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን እንደራሱ ንብረት አድርጎ ሊጠብቅና ወንጀለኞቹን አድኖ በመያዝ ለፀጥታ አካላት በማቅረብ ህገ-ወጦችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋፆ ሊያበረክት ይገባል እንላለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.3K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 15:43:39
ውድ ደንበኞችን ከወቅቱ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ ከሚችል የኤሌክትሪክ #አደጋዎች እራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ !!

ኤሌክትሪክ በዕለት ተዕለት ኑሮችን ላይ እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ካልተደረገ ለአካል ጉዳት፣ ለህይወት መጥፋት እና ለንብረት ውድመት ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ባለማድረግ እራስዎንና ቤተሰብዎን ከኤሌክትሪክ አደጋ ይጠብቁ !!
• ተበጥሶ የወደቀ፣ የተንጠለጠለና ያልተሸፈነ የኤሌክትሪክ ገመድ ወይም ሽቦ ከመነካካት፣
• የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን ከቆሮቆሮ አጥር፣ ከልብስ ማስጫ ሽቦዎች ጋር ከማገናኘት፣
• በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች በቅርብ ርቀት የንግድ ስራ ከማከናወን፣
• ህጻናት በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች በቅርብ ርቀት እንዲጫዎቱ ከመፍቀድ፣
• ውሃ ውስጥ፣ እርጥብ መሬትና ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ነገር ላይ ቆሞ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎቹን ከመነካካት፣
• በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መሳሪያዎች ላይ ቃጠሎ ሲነሳ በውሀ ለማጥፋት ከመሞከር፣
• ያለበቂ እውቀትና ጥንቃቄ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት ከማከናወን፣
• የኤሌክትሪክ መስመሩን ከመቆጣጠሪያው ሳያጠፉ በኤሌክትሪክ የተያዘን ሰው ህይወት ከአደጋ ለማዳን ከመሞከር፣
• የዛፍ ቅርንጫፎችን ሲቆረጡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ እንዲወድቅ ከማድረግ፣

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.8K viewsedited  12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 10:36:25
በአዲስ አበባ ኮቶቤና አካባቢው ለምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን በሙሉ

የኮንስትራክሽን ስራ ሲከናወን አስፈላጊው ጥንቃቄ ባለመደረጉ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት አጋጥሟል።

በመሆኑም ኮተቤ 04፣ ሲቭል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት ወደ ፊጋ አካባቢ፣ አልታድ መስጊድ አካባቢ፣ ሰሚት ልዩ ቤቶች፣ የተባበሩት ማደያ ጀርባ አስከ ፍየል ቤት፣ ሰንሻይን አፓርታማዎች አካባቢ፣ ኮተቤ 09፣ የመብራት ሀይል ጋራጅ መአድን ሚንስትር፣ የስራና ክህሎት ሚንስትር፣ ጆርጅ ዘይት ቤት እሰከ ጃክሮስ ድረስ ያሉ አካባቢዎ በዛሬው እለት የኤሌክትሪክ መቋረጥ አጋጥሟል።

ስለሆነም ጉዳት የደረሠበትን መሠረተ ልማት ጥገና በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አውቃችሁ የጥገና ስራው ተጠናቆ አገልግሎቱ ዳግም እስኪመለስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን ።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.2K viewsedited  07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 16:47:21
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.1K viewsedited  13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 12:21:10
ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የራዲዮ ኮሙዩንኬሽን ፕሮጀክት ስራ በመከናወን ላይ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የውስጥ እና የውጭ አሰራሩን ለማሻሻል የሚያግዝ የሁለተኛው ምዕራፍ የዲጅታል የራዲዮ ኮሙዩንኬሽን ፕሮጀክት ትግበራ በ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በሆነ ወጪ በመከናወን ላይ ነው፡፡

የሬዲዮ ኮሙዩኒኬሽን ፕሮጀክቱ የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴና የአስቸኳይ ጥገና ስራ ቀልጣፋ ለማድረግ፣ ከማከፋፈያ ጣቢያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳለጥ፣ በግንኙነት ክፍተት ሊፈጠሩ የሚችሉ የንብረት እና የሰው አደጋ ለመቀነስ የሚያግዝ ነው፡፡

በተጨማሪም አገልግሎቱ በየደረጃው ያሉ የስራ መሪዎች ስራ ለመምራትና መልዕክት ለማስተላለፍ፣ ችግር ሲያጋጥም በቀጥታ ገብቶ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ፣ የሰራተኞችን እና የደንበኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ከከፍተኛ መስመር ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችንም ቀድሞ ለመከላከል ያስችላል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ምስፈንጠሪየውን ይጫኑ http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/news/detail/484
3.3K viewsedited  09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 10:45:30
በሃይል አጠቃቀም ችግርና ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን #የሃይል ብክነት ለመከላከል ኃይል ቆጣቢ የሆኑ የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎችን ይጠቀሙ፣ የኤሌክትሪክ መጠቀሚያ ዕቃዎችን ኃይል ቆጣቢ መሆናቸውን ያረጋግጡ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ምጣድ፣ ምድጃ፣ ማሽን እና ሌሎች የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎችን በአዳዲስ በመቀየር እና የኃይል ጭነት በማይበዛበት ጊዜ ማለትም ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት በመጠቀም ሊኖር የሚችለውን የሃይል ብክነት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይችላሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
561 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 10:44:31
የኤሌክትሪክ ሃይል #ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት በህግ የሚያስቀጣ መሆኑን ያውቃሉ? እንግዲያውስ የኤሌክትሪክ ለሌላ ሰው ወይም ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት በኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006/ አንቀፅ 29/9 በህግ ያስቀጣል ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሃይል የሰረቀ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ከሌላ ጋር ያገናኘ፣ መስመር ያሰናከለ ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል ኢንዲሰረቅ ከሌላ መስመር ጋር እንዲገናኝ ወይም መስመሩ እንዲሰናከል ያደረገ ወይም መስመሩ የተሰረቀ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሌላ መስመር ጋር የተገናኘ ወይም የተሰናከለ መሆኑ እያወቀ ከዚሁ መስመር ለፍጆታ ያዋለ ወይም የተገለገለ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.3K viewsedited  07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 16:38:44
በመዲናዋ በአንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው

ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት በሃምሳ የኤሌክትሪክ መጋቢ መስመሮች ላይ ብልሽት አጋጥሞ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች አገልግሎቱ ተቋርጦ መቆየቱን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዲስትሪቢዩሽን መቆጣጠሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ ባሳዝነው መኮንን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው መጋቢ መስመሮች ተጠግነው አገልግሎቱን ወደ ነበረበት መመለስሱን የጠቀሱት ኃላፊው ቀሪዎቹ አካባቢዎችን በፍጥነት ለማገኛኘት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እንደነዚህ አይነት መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ የቅድመ ጥገና ስራዎች በሰፊው እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው፣ በቀጣይ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የማሰራጫ መስመሮች ማሻሻያ ፕሮጀክት ተጠናቆ ስራ ሲጀምር ችግሩ ሙሉ ለሙሉ የሚቀረፍ ይሆናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ የዛፎች አለመቆረጥ ለሃይል መቆራረጥ መንስዔ ስለሚሆን ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የሚነካ ዛፍ በሚኖርበት ወቅት በአካባቢው ለሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በማሳውቅ ሊያስወግድ ይገባል ብለዋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.2K viewsedited  13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 12:33:19
የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እየተከናወነ የሚገኘው የለውጥ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እያከናወናቸው የሚገኙት የለውጥ እንቅስቃሴዎች አበረታች መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ፕሮፌሰር ኢ/ር መሐመድ አብዶ ገልፀዋል፡፡

ሰብሳቢው አክለውም ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ በማዋል፣ የማሰራጫ መስመሮችን አቅም በማሳደግ፣ የአገልግሎቱን ተደራሽነትን በማረጋገጥ እና በመሳሰሉት ተግባራት ረገድ እያስመዘገበ ያለው ለውጥ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን እውን ለማድረግ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ይጠበቅበታል ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገሪቱን ዕድገት እውን ለማድረግ የላቀ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ህብረተሰቡ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀመውን ስርቆት በመከላከል ሊያግዝ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራ ተሊላ በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ ለመገንዘብ ላደረገው ጥረት ምስጋና አቅርበው የተሰጡ ግብረ መልሶች ስራ ላይ እንዲውሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው አገልግሎቱ እያከናወነ የሚገኘውን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ትግበራ አቃቂ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ፣ ጎፋ የሚገኘውን መረጃ ማዕከልና ማዕከላዊ የዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርጓል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.7K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 21:05:57
ለማሰራጫ መስመሮች አቅም ማሻሻል ስራ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል - ቋሚ ኮሚቴው

በአገሪቱ በሀይል ማመንጨት ዘርፍ የተገኘውን መልካም ውጤት በማሰራጫ መስመሮች ግንባታና ማሻሻልም እውን ለማድረግ ትልቅ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት አስታወቁ፡፡

ይህ የተገለፀው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች ጋር ለሁለት ቀናት እየተካሄደ ባለው ምክክር ላይ ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ተቋሙ በርካታ ሃላፊነቶች በመቀበል አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ለማዳረስ እንዲሁም ህብረተሰቡን በቅርበት ለማገልገል የሚያደርገው ጥረት የሚያበረታ ነው ብለዋል፡፡

የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ፣ ክፍያ ከፍለው አገልግሎት የሚጠብቁ ደንበኞች መኖር፣ የተዘረጉ መስመሮች አንዳንድ ቦታዎች ላይ አገልግሎት ያለመስጠት፣ በተቋሙ ገቢ አሰባሰብ ላይ ክፍተት መኖር፣ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ መዘግየት መስተዋል፣ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክፍተት መኖር የመሳሰሉ ችግሮች ሊቀረፉ እንደሚገባ ተገጿል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.0K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ