Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ በአንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ | Ethiopian Electric Utility

በመዲናዋ በአንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው

ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት በሃምሳ የኤሌክትሪክ መጋቢ መስመሮች ላይ ብልሽት አጋጥሞ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች አገልግሎቱ ተቋርጦ መቆየቱን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዲስትሪቢዩሽን መቆጣጠሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ ባሳዝነው መኮንን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው መጋቢ መስመሮች ተጠግነው አገልግሎቱን ወደ ነበረበት መመለስሱን የጠቀሱት ኃላፊው ቀሪዎቹ አካባቢዎችን በፍጥነት ለማገኛኘት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እንደነዚህ አይነት መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ የቅድመ ጥገና ስራዎች በሰፊው እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው፣ በቀጣይ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የማሰራጫ መስመሮች ማሻሻያ ፕሮጀክት ተጠናቆ ስራ ሲጀምር ችግሩ ሙሉ ለሙሉ የሚቀረፍ ይሆናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ የዛፎች አለመቆረጥ ለሃይል መቆራረጥ መንስዔ ስለሚሆን ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የሚነካ ዛፍ በሚኖርበት ወቅት በአካባቢው ለሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በማሳውቅ ሊያስወግድ ይገባል ብለዋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et