Get Mystery Box with random crypto!

የኤሌክትሪክ ሃይል #ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት በህግ የሚያስቀጣ መሆኑን ያውቃሉ? እንግዲያውስ | Ethiopian Electric Utility

የኤሌክትሪክ ሃይል #ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት በህግ የሚያስቀጣ መሆኑን ያውቃሉ? እንግዲያውስ የኤሌክትሪክ ለሌላ ሰው ወይም ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት በኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006/ አንቀፅ 29/9 በህግ ያስቀጣል ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሃይል የሰረቀ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ከሌላ ጋር ያገናኘ፣ መስመር ያሰናከለ ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል ኢንዲሰረቅ ከሌላ መስመር ጋር እንዲገናኝ ወይም መስመሩ እንዲሰናከል ያደረገ ወይም መስመሩ የተሰረቀ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሌላ መስመር ጋር የተገናኘ ወይም የተሰናከለ መሆኑ እያወቀ ከዚሁ መስመር ለፍጆታ ያዋለ ወይም የተገለገለ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et