Get Mystery Box with random crypto!

የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እየተከናወነ የሚገኘው የለውጥ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑ ተገለፀ | Ethiopian Electric Utility

የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እየተከናወነ የሚገኘው የለውጥ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እያከናወናቸው የሚገኙት የለውጥ እንቅስቃሴዎች አበረታች መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ፕሮፌሰር ኢ/ር መሐመድ አብዶ ገልፀዋል፡፡

ሰብሳቢው አክለውም ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ በማዋል፣ የማሰራጫ መስመሮችን አቅም በማሳደግ፣ የአገልግሎቱን ተደራሽነትን በማረጋገጥ እና በመሳሰሉት ተግባራት ረገድ እያስመዘገበ ያለው ለውጥ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን እውን ለማድረግ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ይጠበቅበታል ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገሪቱን ዕድገት እውን ለማድረግ የላቀ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ህብረተሰቡ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀመውን ስርቆት በመከላከል ሊያግዝ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራ ተሊላ በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ ለመገንዘብ ላደረገው ጥረት ምስጋና አቅርበው የተሰጡ ግብረ መልሶች ስራ ላይ እንዲውሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው አገልግሎቱ እያከናወነ የሚገኘውን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ትግበራ አቃቂ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ፣ ጎፋ የሚገኘውን መረጃ ማዕከልና ማዕከላዊ የዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርጓል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et