Get Mystery Box with random crypto!

ለማሰራጫ መስመሮች አቅም ማሻሻል ስራ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል - ቋሚ ኮሚቴው በአገሪቱ በሀይ | Ethiopian Electric Utility

ለማሰራጫ መስመሮች አቅም ማሻሻል ስራ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል - ቋሚ ኮሚቴው

በአገሪቱ በሀይል ማመንጨት ዘርፍ የተገኘውን መልካም ውጤት በማሰራጫ መስመሮች ግንባታና ማሻሻልም እውን ለማድረግ ትልቅ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት አስታወቁ፡፡

ይህ የተገለፀው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች ጋር ለሁለት ቀናት እየተካሄደ ባለው ምክክር ላይ ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ተቋሙ በርካታ ሃላፊነቶች በመቀበል አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ለማዳረስ እንዲሁም ህብረተሰቡን በቅርበት ለማገልገል የሚያደርገው ጥረት የሚያበረታ ነው ብለዋል፡፡

የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ፣ ክፍያ ከፍለው አገልግሎት የሚጠብቁ ደንበኞች መኖር፣ የተዘረጉ መስመሮች አንዳንድ ቦታዎች ላይ አገልግሎት ያለመስጠት፣ በተቋሙ ገቢ አሰባሰብ ላይ ክፍተት መኖር፣ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ መዘግየት መስተዋል፣ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክፍተት መኖር የመሳሰሉ ችግሮች ሊቀረፉ እንደሚገባ ተገጿል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et