Get Mystery Box with random crypto!

በሶማሌ ክልል ስምንት ከተሞች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ በሶማሌ ክልል ስም | Ethiopian Electric Utility

በሶማሌ ክልል ስምንት ከተሞች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ

በሶማሌ ክልል ስምንት የዞን እና ወረዳ ከተሞች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ።

የአገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት ከተሞች ዶሎ፣ ቆረሃይ፣ ሸበሌና ፋፈን ዞኖች የሚገኙ ዋርዴር፣ ኩዱንቡር፣ ይዒብ፣ ገርሎጉበይ፣ ዋፍዱብ ኢልሓር፣ በራጂሳሌ እና አፉፍሌይ ናቸው ።

በኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት የሶማሌ ክልልፕሮጀክት አስተዳደር ኃላፊ አቶ አሊ ሰዒድ ከመንግስት በተመደበ 200 ሚሊዮን ብር ባለፉት ስድስት ወራት የሙሉ ቀን የኤሌትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

እንደ አቶ አሊ ሰዒድ ገለጻ 18 ትራስፎርመርም ፣ 207 ኪሎ ሜትር መስመር በመዘርጋት እና 2 ሺህ 217 ምሶሶ ተከላ ስራ ተከናውኗል።

የኃይል አቅርቦቱን በሌሎች 11 ከተሞች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et