Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.33K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-03-07 11:23:41
የ25 የገጠር ከተሞች የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻፀም 24.1 በመቶ ደረሰ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት እውን ለማድረግ በተቀረፀው ብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፍኖተ ካርታ መሰረት ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ 25 የገጠር ከተሞችን በፀሃይ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ የአፍሪካ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲሆኑ፤ አጠቃላይ ወጪው 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 161 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በስምንት ክልሎች በተመረጡ የገጠር ከተሞች በመገንባት ላይ ሲሆን፤ በ6 ሎት ተከፍሎ በአራት ኮንትራክተሮች በመከናወን ላይ ነው፤ አጠቃላይ አፈጻፀሙም 24.1 በመቶ ደርሷል፡፡

በግንባታ 2.84 ኪ.ሜ የመካከለኛ ሃይል መስመር 16.91 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እና 4 ትራንስፎርመሮች ተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡

8 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ፕሮጀክት፤ 68 ነጥብ 7 የመካከለኛና 233 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ይከናወንበታል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የዕውቀት ሽግግርንና ሰፊ የስራ ዕድል የሚፍጥር ሲሆን፤145 ሺህ 169 አዳዲስ ደንበኞችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
2.4K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:54:57 ቀልጣፋና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተግባራዊ እያደረገው በሚገኘው የሶስት አመት በስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት የተሳለጠ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለመስጠት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ገልፀዋል፡፡

ይህ የተገለፀው ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ተቋሙ ከቁልፍ ደንበኞችንና ባለድርሻ አካላትን ጋር በሂልተን ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደ የግማሽ ቀን ምክክር መድርክ ላይ ነው፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው ስትራቴጂ ዕቅድ መሰረት ለደንበኞች ቀልጣፋና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የመተግበር፣አገልግሎቱን የማስፋፋት፣ መሰረተ-ልማትን የማሻሻል የመሳሰሉ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሀይል መቆራረጥና መዋዥቅ፣ የሰራተኞች ስነ-ምግባር ችግር፣ የመሰረተ ልማት ስርቆት፣ የአስቸኳይ ጥገና አገልግሎት መዘግየት፣ የንባብ ችግር፣ ለኢንዱስትሪ ደንበኞች ተገቢው ትኩረት አለመስጠት፣ የፓወር ፋከተር ኮሬክተር አጠቃቀም ችግር እና የማከፋፈያ ጣቢዎች አቅም መዳከም ችግር እንደሚስተዋል ጠቁመዋል፡፡

የተቋሙ ኃላፊዎች በበኩላቸው በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለማስወገድ የሚያስችሉ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ዝርጋታ፣ አዲስ የጥሪ ማዕከል ግንባታ፣ የሰራተኞ የስነ-ምግባርና የአቅም ችግሮችን መቅርፍ፣ አዳዲስ የክፍያ አማራጮችን መዘርጋት፣ የማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቅም የማሳደግ እና ሌሎች ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.5K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:54:08
2.4K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:54:07
2.3K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 10:08:13
በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በተገዙ የኤሌክትሪክ #መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆትና ውድመት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተፅኖ ከማሳደሩም በላይ በቴሌ ኮሚኒኬሽንና የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 464/97 መሰረት በህግ ያስጠይቃል፡፡

አዋጁን ተላልፎ ድርጊቱን የፈፀመ ማንኛውም አካል ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት የሚቀጣ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ይህን መሰል እኩይ ተግባር የምትፈፅሙ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን፤ በየደረጃው የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍልም ቢሆን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን እንደራሱ ንብረት አድረጎ ሊጠብቅና በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱና ስርቆ የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ሊመለከት በአካባቢው ለሚገኝ የፀጥታ አካላት በማሳወቅ ሃገራዊ ሃላፊነታችንን ሊወጣ ይገባል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.0K viewsedited  07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 15:14:26
በሰባት ከተሞች የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ግንባታ ሊያከናውን ነው

የሶማሌ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በክልሉ በሚገኙ ሰባት ከተሞች የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ግንባታ ሊያከናውን መሆኑ ተገለፀ፡፡

ግንባታው በሞያሌ(2) ፣ ፊልቱ፣ ሺኒሌ፣ ፋፋን፣ ሃርቲሼክ፣ ማርማሳ፣ ዱርዋሌ እና አራርሶ ከተሞች ሲሆን ግንባታው በበጀት ዓመቱ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ከዚህ በፊት ከተሞቹ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የከተሞቹን በፍጥነት ማደግ ተከትሎ የህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ የማስፋፊያ ግንባታ ማከናወን አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የሶማሌ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለግንባታው ግብዓት የሚሆኑ ሰባት ትራንስፎርመሮችን ገዝቶ ያቀረበ ሲሆን ቀሪውን ስራዎችን ለማከናወን 20 ሚሊዮን 150 ሺ 645 ብር ከ14 ሳንቲም በሆነ ወጪ ለማከናወን ከሶማሌ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ሰሞኑን ተፈራርሟል፡፡

በግንባታው የሰባት ከ200 እስከ 315 ኬ.ቪ.ኤ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ተከላ፣ 6 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመርና 21 ነጥብ 4 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ይከናወናል፡፡

ይህ የማስፋፊያ ግንባታ ሲጠናቀቅ የከተሞቹን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማሳደግ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
3.1K viewsedited  12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 10:55:18
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጠ ማሳሰቢያ

እሁድ የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፤ በወራቤ፣ በኮስቲክት ሶዳ፣ በመቂ አለምጤና፣ በቡታጅራ፣ በኢንዱስትሪ፣ በኬላ፣ በአዳሚቱ፣ በዝዋይ፣ በመቂ፣ በቡልቡላ፣ በኮርሜ፣ በአሉቶ፣ በሸልዋሾ፣ በቡኢ እና አካባቢዎቻቸው ለከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጥገና ስራ ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
3.7K viewsedited  07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 18:37:46
የተርፋም ቀበሌ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነች

በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዮ ወረዳ የምትገኘው ተርፋም ቀበሌ የኤሌትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነች።

ከጋምቤላ ከተማ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በ41 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምተገኝው ተርፋም ቀበሌ የረጅም ጊዜ የሃይል ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ ህብረተሰቡ ደስተኛ መሆኑን የቀበሌዋ አስተዳዳሪ አቶ ተኛል ኮክ ተናግረዋል፡፡

ቀበሌዋን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ 0.3 ኪ.ሜ መካከለኛና 6.45 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ ሲሆን ሁሉም መስመሮች በኮንክሪት መሶሶ እንዲገነቡ ተደርጓል፡፡

ግንባታው በጋምቤላ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገር አቀፍ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ኘሮግራም በራስ ሃይል የተከናወነ ሲሆን በግንባታው ሁለት ባለ 200 ኬ.ቪ.ኤ ትራንስፎርመሮች ተተክለዋል።

ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ 212 የነጠላና የሶስት ፌዝ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የቻሉ ሲሆን በርካታ ነዋሪዎች ደግሞ ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

በቅርቡም የግንባታው ርክክብ በመደረጉ ባለ ሶስት ፌዝ እና ባለ ነጠላ ፌዝ ቆጣሪ አገልግሎት ጠያቂዎች በኢታንግ ደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከል በኩል የሚስተናገዱ ይሆናል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
2.2K viewsedited  15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 09:46:13
እንኳን ለ127ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
4.0K viewsedited  06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 15:15:06
አዲሱ #ስማርት የኤሌክትሪክ ቆጣሪ

ተቋሙ በደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን ከግምት በማስገባት እንዲሁም የቆጣሪ ደኅንነት ጠቀሜታን በማጤን ዘመናዊ ቆጣሪ (Smart Meter) እየገጠመ ይገኛል፡፡

ቆጣሪው ባሉት ዘመናዊ ቴክኖሎጂና ባህሪ ላይ ከተጠቀሱት የቆጣሪ ዓይነቶች ይለያል፡፡ አሁን ባለው ሂደት ቆጣሪዎቹ ለክፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች እየተገጠሙ ይገኛል፡፡ በሂደት ለመካከለኛ እና ለዝቅተኛ ኃይል ተጠቃሚዎች ደንበኞች ለማዳረስ እየተሰራ ይገኛል፡፡

አዲሶቹ ስማርት ቆጣሪዎች በርከት ያሉ ጠቀሜታዎች አሏቸው ከነዚህም መካከል፡- ለደንበኛው የተጠቀመውን የኃይል መጠን በየወቅቱ መረጃ ይሰጣሉ፤ ከማዕከል ያለ አንባቢ የፍጆት መጠን እንዲነበብ ያስችላሉ፤ ከተቋሙ እውቅና ውጪ ቢነካኩ ለመከታተልና ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡

በተጨማሪም በንባብ መዘግየት ምክንያት የሚነሱ ቅሬታዎች እና በግምት የሚሞሉ አሠራሮችን ያስቀራሉ፤ በአንባቢ የሚፈጠሩ ስህተቶችን የሚቀርፍ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ዝርዝር መረጃዎቻችን ለማግኘት ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.2K viewsedited  12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ