Get Mystery Box with random crypto!

የ25 የገጠር ከተሞች የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻፀም 24.1 በመቶ ደረሰ የኢትዮጵያ | Ethiopian Electric Utility

የ25 የገጠር ከተሞች የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻፀም 24.1 በመቶ ደረሰ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት እውን ለማድረግ በተቀረፀው ብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፍኖተ ካርታ መሰረት ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ 25 የገጠር ከተሞችን በፀሃይ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ የአፍሪካ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲሆኑ፤ አጠቃላይ ወጪው 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 161 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በስምንት ክልሎች በተመረጡ የገጠር ከተሞች በመገንባት ላይ ሲሆን፤ በ6 ሎት ተከፍሎ በአራት ኮንትራክተሮች በመከናወን ላይ ነው፤ አጠቃላይ አፈጻፀሙም 24.1 በመቶ ደርሷል፡፡

በግንባታ 2.84 ኪ.ሜ የመካከለኛ ሃይል መስመር 16.91 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እና 4 ትራንስፎርመሮች ተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡

8 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ፕሮጀክት፤ 68 ነጥብ 7 የመካከለኛና 233 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ይከናወንበታል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የዕውቀት ሽግግርንና ሰፊ የስራ ዕድል የሚፍጥር ሲሆን፤145 ሺህ 169 አዳዲስ ደንበኞችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et