Get Mystery Box with random crypto!

ቀልጣፋና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ የኢትዮጵያ ኤ | Ethiopian Electric Utility

ቀልጣፋና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተግባራዊ እያደረገው በሚገኘው የሶስት አመት በስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት የተሳለጠ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለመስጠት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ገልፀዋል፡፡

ይህ የተገለፀው ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ተቋሙ ከቁልፍ ደንበኞችንና ባለድርሻ አካላትን ጋር በሂልተን ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደ የግማሽ ቀን ምክክር መድርክ ላይ ነው፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው ስትራቴጂ ዕቅድ መሰረት ለደንበኞች ቀልጣፋና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የመተግበር፣አገልግሎቱን የማስፋፋት፣ መሰረተ-ልማትን የማሻሻል የመሳሰሉ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሀይል መቆራረጥና መዋዥቅ፣ የሰራተኞች ስነ-ምግባር ችግር፣ የመሰረተ ልማት ስርቆት፣ የአስቸኳይ ጥገና አገልግሎት መዘግየት፣ የንባብ ችግር፣ ለኢንዱስትሪ ደንበኞች ተገቢው ትኩረት አለመስጠት፣ የፓወር ፋከተር ኮሬክተር አጠቃቀም ችግር እና የማከፋፈያ ጣቢዎች አቅም መዳከም ችግር እንደሚስተዋል ጠቁመዋል፡፡

የተቋሙ ኃላፊዎች በበኩላቸው በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለማስወገድ የሚያስችሉ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ዝርጋታ፣ አዲስ የጥሪ ማዕከል ግንባታ፣ የሰራተኞ የስነ-ምግባርና የአቅም ችግሮችን መቅርፍ፣ አዳዲስ የክፍያ አማራጮችን መዘርጋት፣ የማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቅም የማሳደግ እና ሌሎች ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et