Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-03-24 09:24:22
በሀዋሳ ከተማ በአጋንሳ መንደር 454 አባወራዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ በቱላ ክፍለ ከተማ በዳቶ ቀበሌ ሲከናወን የነበረው የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራ በመጠናቀቁ 454 አባወራዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

በተከናወነው የኤሌክትሪክ የማስፋፊያ ስራ አንድ ባለ 630 እና አንድ 800 ኪ.ቪ ትራንስፎርመሮችን ፣ 307 የኤሌክትሪክ ምሶሶዎች፣ 6.7 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እና 0.2 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ስራ ተከናውኗል፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጄክቱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

በተመሳሳይ የግንባታ ስራቸው ተጠናቆ በኮሚሺኒንግ ስራ ላይ ያሉ 10 ፕሮጄክቶች ያሉ ሲሆን በቀጣይ ለአዲስ ደንበኞች አገልግሎት መስጠት የሚጀምሩ ይሆናል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.0K views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 14:45:45
በሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ስር ለምትገኙ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ

የሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ከዚህ በፊት በአራት ምድብ ሲጠቀምበት የነበረውን የንባብ እና የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ መክፍያ የጊዜ ሰሌዳ ወደ አንድ ለማምጣት ከመጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ መርሃ-ግብር በስራ ላይ አውሏል፡፡

በዚሁም መሰረት ወር በገባ ከ13ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 26ኛው ቀን ድረስ የንባብ ጊዜ ሲሆን ወር በገባ ከ28ኛው ቀን እስከሚቀጥለው ወር 4ኛ ቀን ድረስ ደግሞ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ መክፈያ የጊዜ ሰሌዳ እንዲሆን አድርጓል፡፡

ስለሆነም በዲስትሪክቱ ስር የምተገኙ ደንበኞቻችን ይህንኑ አውቃችሁ ለቆጣሪ አንባቢዎች የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደርጉና ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባችሁን ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ማለትም በቴሌ ብር፣ ሞባይል ባንኪንግ፣ ሲ.ቢ.ኢ ብር እና በኢንተርኔት ባንኪንግ እንድትፈፅሙ እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.3K viewsedited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 13:08:02
260 የመካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ 260 የመካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

ኢንዱስትሪዎቹ የተገነቡት በቃሊቲ ወርቁ ሰፈርና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢዎች ሲሆን ሁሉም የኢንዱስትሪ ሸዶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

ሸዶቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያየ አቅም ያላቸው ሰባት ትራንስፎርመሮች እና 283 የዝቅተኛ መስመር መሰሶዎች ተተክለዋል፡፡

በተጨማሪም 230 ቆጣሪዎች የተገጠሙ ሲሆን 400 ሜትር የመካከለኛ መስመርና 10 ነጥብ 8 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡

ግንባታውን ለማከናወን 12 ሚሊየን 673 ሺህ 383 ወጪ የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ኢንዱስትሪዎቹ ምርት በማምረት ላይ
ይገኛሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.7K views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 12:29:12
ለጥገና ሥራ ሲባል የሚቋረጥ ሃይል አቅርቦት

የሃረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሀሙስ መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ስዓት እስከ ቀኑ 8 ሰዓት ድረስ በነርሲስግ ኮንዶሚኒም፣ በኖክ፣ በሞቢል፣ በኤርር በር፣ በስንጋ በር፣ በኤረር ወረዳና አካባቢው የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱ አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ ተገንዝባችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.7K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 11:49:04
400 አባወራዎችን ተጠቃሚ ለሚያደርግ የመስኖ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ስራ ተከናወነ

በሀረሪ ክልል 400 አባወራዎችን ተጠቃሚ ለሚያደርግ የመስኖ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራ ተከናወነ፡፡

በ9 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የተገነባው ይህ ኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ወጪው ሙሉ በሙሉ የተሸፈነው በሀረሪ ክልል መንግስት ነው፡፡ በግንባታው 1.2 ኪሜ ከፍተኛ መስመር እና 9.1 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ስራ ተከናውኗል፡፡

የኤሌክትሪክ መስመሩ በመገንባቱ የአካባቢውን ልማት በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግና ለማዘመን እንደሚያግዝ የአካባቢው አርሶ አደሮች ገልፀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአካባቢው ያለውን የውሀ ሀብት ለማልማት የሚያስችል ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአካባቢው እየተመረተ ያለውን የእህል ሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት በከፍተኛ ደረጃ የሚጨምር ነው፡፡
ፕሮጅክቱም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.0K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 15:36:59
በመዲናዋ ለሁለት ሳምንታት ተከስቶ የነበረው የሃይል መቆራረጥ ችግር በተደረገው ጥገና ወደነበረበት መመለሱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሁለት ሳምንታት ተከስቶ የቆው የሃይል መቆራረጥ ችግር በተደረገው አፋጣኝ ጥገና አገልግሎቱ ወደ ነበረበት መመለሱን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ገበየሁ ሊካሳ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ስራ አስፈጻሚው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ባለፉት ሁለት ሳመንታት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በግንባታ ፕሮጀክቶች፣ በአረጁ መስመሮች ላይ በደረሰ ጉዳት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሃይል መቆራረጥ ችግር ሲያጋጥም መቆየቱን ገልፀው ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

ችግሩን ለመፋታት በተደረገ ርብርብ ፈጣን ጥገናዎችን በማካሄድ አገልግሎቱን ወደነበረበት መመለስ መቻሉን እና በአንዳንድ የሃይል መቆራረጥ ችግር በሚስተዋልባቸውን መስመሮችንና የማከፋፈያ ጣቢያዎች የመጠገንና የግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገበየሁ ሊካሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.8K viewsedited  12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 12:36:08
ውድ ደንበኛችን የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ካሉበት ሆነው መክፍል ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ተቋሙ በዘረጋቸው #ቀላልና ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ይክፍሉ! ይህን ሲያደርጉ አስፈላጊ ካልሆነ ወጪና እንግልት ያድናሉ! ኑሮንም ያቃልላሉ! በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመምጣት ጊዜዎትን፣ ጉልበትዎትንና ገንዘብዎትን አያባክኑ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.8K viewsedited  09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 11:41:06
በኮንታና ዳውሮ ዞኖች የምትገኙ ደንበኞቻችን

ከመጋቢት 06 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በዳውሮ ዞን አባ ከተማ ላይ በሚገኝ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ በደረሰ ብልሽት በዳውሮ እና በኮንታ ዞን ባሉ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦል፡፡

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን በጅማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሰራተኞች በማከፋፈያ ጣቢያው የደረሰውን ብልሽት አስተካክለው እንደጨረሱ በፍጥነት አገልግሎቱን የምንሰጥ መሆኑን አውቃችሁ በትግስት
እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
1.6K viewsedited  08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 15:20:20

2.4K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 12:20:47
የመኖሪያ ቤት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኛ ከሆኑ፤ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳቦትን በቀላሉ ለማስላት ያመችዎት ዘንድ ይህንን #የታሪፍ_መረጃ ይጠቀሙ፡፡ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎትንም ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ቀኑን ጠብቀው ይፈፅሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.4K viewsedited  09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ