Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 43

2022-07-16 10:11:57 ስፖርት ክለቡ ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ
******************
የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የብራንድ ትጥቅ አቅራቢነት ስፖንሰርሺፕ ስምምነት ትላንት በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ተፈራርሟል፡፡

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮ- ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጫላ አማን እና የጎፈሬ ትጥቅ አምራች ደርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል መኮንን ናቸው።

ለሶስት አመት በሚቆየው በዚህ ስምምነትም፤ ለወንዶች እና ለሴቶች ዋና ቡድን፣ ለ21 ዓመትና ለ17 ዓመት በታች ቡድኖች እንዲሁም ክለቡን ወክለው በተለያየ የስፖርት ዘርፍ ለሚሳተፉ የክለቡ አባላት ድርጅቱ ትጥቅ እንሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጫላ አማን በዚህ ወቅት፡- ስምምነቱ የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረትና የሀገር በቀል ምርት የሚያቀርቡ የትጥቅ አምራች ድረጅቶችን ለማበረታታት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ድርጅቱም የተመረጠውም የኢትዮ-ኤሌክትሪክን ክብርና አንጋፋነት የሚመጥን ምርት ማቅረብ የሚችል መሆኑን በመረጋገጡ ነው ብለዋል፡፡

የጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል መኮንን በበኩላቸው ድርጅታቸው ለአራት ዓመታት ያክል በኢትዮጵያ ውስጥ እና በውጭ ሃገር ከሚገኙ የስፖርት ክለቦች ጋር በኮንትራትና በግዢ በሚደረጉ ስምምነቶች ትጥቅ እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብም ጋር የተፈረመው ስምምነት የዚህ አንድ አካል እንደሆነና ልዩ የሚያደረገውም ለሶስት ዓመታት በቋሚነት የሚቆይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም በስምምነቱ ላይ ከትጥቅ አቅርቦት በተጨማሪ ለአስልጣኞች፣ ለተጫዋቾችና ለደጋፊዎች የተለያዩ የእውቀት ደረጃን ለማሳደግ የሚረዱ ስልጠናዎችን ጎፈሬ ድርጅት እንደሚያመቻችና እንደሚያዘጋጅ በስምምነቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም አንጋፋውን የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ደጋፊ ማህበር ለማበረታት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ጫላ፤ ለደጋፊዎች የሚሆን መለያዎችም እየተዘጋጁ እንደሆነ እና በቅርብ ቀን ለገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን በዕለቱ ክለቡ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የክፍሌ ቦልተናን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት አራዝሟል፡፡

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ እጅጉ እና አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ናቸው።

የሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ባለቤቱ አይበገሬውና አንጋፋው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እግር ኳስ ክለብ፣ በአንጋፈው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና እየተመራ የ2014 የከፍተኛ ሊግ የምድብ "ሀ" አሸናፊ በመሆን ፕሪሜየር ሊጉን ከ አራት ዓመታት በኋላ ዘንደሮ መቀላቀሉ ሚታወስ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.3K viewsedited  07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 10:11:57
2.5K views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 10:50:17
በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኤሌክትሪክ አቅርቦት /በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች/
********************
በሮቤ ሰብሰቴሽን ባጋጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በሮቤ፣ በአጋርፋ፣ በሲና ከተማና አካባቢያቸው በከፊል እንዲሁም ጋሰራ ከተማና አካባቢው ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

ወቅቱ ከባድ ዝናብ የሚጥልበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጥገና ስራው አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ችግሩ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ አፋጣኝ እልባት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በአካባቢዎቹ የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን፤ የጥገና ሥራው ተጠናቆ ችግሩ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
5.3K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 09:03:43 በፕሮጀክቶች የአፈጻፀም ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቀነስ የሚያስችሉ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ተገለፀ
*****************************
በፕሮጀክቶች የአፈጻፀም ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቀነስ የሚያስችሉ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ለምልም ምስጋናው ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሯ ይህን የገለፁት ከሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሶሰት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በቆየው የ2014 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማና የ2015 በጀት አመት ዕቅድ ውይይት ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡

በዕቅድ አፈጻፀም ግምገማው የማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት ወ/ሮ ለምለም ከፕሮጀክት አፈጻፀም ጋር የተያያዙ ችግሮች ለመፍታና የሚከናወኑፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ተገቢ የሆነ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ማከናወንና ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዳይሬክተሯ አክለውም በኦፍ ግሪድ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ መጓተቶች በተለይም ደግሞ በ12 አነስተኛ የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ላይ ያሉ ቀሪ ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚገባና ለፕሮጀክቶች መጓተት እንደ ምክንያት የሚቀርቡ የፀጥታ ችግሮች ትክክለኛ መሆንና አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

ከኮንክሪት የፖል አቅርቦት ጋር ተያይዞ ችግርሮችን ለመፍታት የአምራቾችን አቅም ባገነዘበ መልኩ ግዥ በመፈፀም ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የኮንሰንትሪክ ኬብል እጥረት ችግርን ለመፍታት በራሳቸው አቅም ማቅረብ ለሚችሉ ደንበኞች እድሉን እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ የገለፁት ዳይሬክተሯ በራሳቸው ማቅረብ ለማይችሉ ደንበኞች በተቋሙ በኩል ሊሠሩ የሚችሉ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ማስተናገድ እንደሚገባም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ከዋናው የኃይል ቋት እስከ 2.5 ኪሜ ርቀት ላይ ለሚገኙ ከተሞች የትራንስፎርመር እጥረት ከታየ የሶይል ትራንስፎርመር በአማራጭነት መጠቀም እንደሚያስፈልግም መመሪያ ተሰጥተዋል፡፡

ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በየደረጃው ከሚገኙ የክልልና የከተማ መስተዳደር አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የክልል ቢሮዎች ከሚያወጧቸው ወጪዎች ጋር የሚመጣጠን ስራ ሊያከናውኑ እንደሚገባና ከንብረት ብክነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመከላከልም ተገቢ የሆነ ክትትልና ቁጥር ሊደርጉ እደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ፒራሚድ ሆቴልና ሪዞርት ሲያካሂድ የቆየው የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት የ2014 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማና የ2015 በጀት አመት ዕቅድ ውይይት በበጀት አመቱ የታዪ ጠንካራና ደካማ ጎናችን በመለየትና በቀጣይ የተሻለ ስራ ለማከናወን የሚያስችሉ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.0K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 09:03:40
3.8K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 10:42:52
በዚህ የክረምት ወቅት ወርሃዊ ክፍያ ለመፈፀም ብለው ስለምን ይጉላላሉ?
******************
ወድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን፡- በዚህ የክረምት ወቅት ወርሃዊ ክፍያ ለመፈፀም ብለው ስለምን ይጉላላሉ? ሳይንከራተቱ፤ ሳይጉላሉ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎን ካሉበት ሆነው በቀላሉ በቴሌብር፣ በ CBE Birr /707070/፣ በሞባይል ባንኪንግና በኢንተርኔት ባንኪንግ ይክፈሉ!

እነዚህን ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ተጠቅመው ክፍያዎትን በመፈፀም ካላስፈላጊ ወጪ ይዳኑ! ኑሮዎትንም ያቅልሉ!

በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን መምጣት ጊዜዎን፣ ጉልበትዎንና ገንዘብዎን ማባከን መሆኑን ይረዱ፡፡ ካሉበት ሆነው ቀላል አማራጭ ብቻ ይጠቀሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
6.6K views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:53:15
አስደሳች ዜና ለክቡራን ደንበኞቻችን!!!
***************
ተቋማችን የደንበኞቹን ፋላጎት ለማርካት ከሀምሌ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ በተጨማሪ ዘወትር ቅዳሜ ግማሽ ቀን መደበኛ የሥራ ሰዓት አድርጓል፡፡

በመሆኑም ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ በቋሚነት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ተገንዝባችሁ፤ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ በሁሉም የተቋሙ ቢሮዎች መገልገል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
7.4K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:46:20 በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ነው
**********************
በዲስትረቡሽን መስመሮች እርጅና ምክንያት በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የዲስትሪቡሽን መስመሮች መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡

በፕሮጀክት ዳይሬክቶሬቱ የዲስትሪቢዩሽን ሪሃቢሊቴሽን ፕሮግራም ጽ/ቤት ተደጋጋሚ የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት የተለያዩ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና በዚህም እየጨመረ ከመጣው የሃይል ፍላጎት ጋር አብሮ የሚሄድ አስተማማኛ የዲስትሪቢዩሽን መስመር በመገንባ በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር መቀነስ መቻሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂናት ለመፍታት ተግባራዊ እየተደረጉ ከሚገኙ የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክቶች መካከል የአዲስ አበባ ዲስትሪቢዩሽን የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት፣ የስድስቱ ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት፣ የአዲስ አበባ ትራንስሚሽንና ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና የአቅም ማሳደግ ፕሮጀክት፣ የ10 ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች እና ሌሎች ፕሮጀክቶችም እንደሚገኙበት ተገልፃል፡፡

በቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር እየተከናወነ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዲስትሪቢዩሽን የመልሶ ግንባታና የአቅም ማሳደግ ፕሮጀክት የፊዚካል ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የማስተካከያ ስራዎች፣ የቴስትና ኮሚሽኒንግ እና የርክክብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡

በአፍሪካ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ እየተከናወነ የሚገኘው የአዲስ አበባ ትራንስሚሽንና ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታ እና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት 52.75 በመቶ መጠናቀቁንና ከመረጃ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ወይም ስካዳ ሲስተም በስተቀር ፕሮጀክቱን በሚቀጥለው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ የእቅድ ክለሳ መደረጉን ተመላክቷል፡፡

የ6ቱ ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት አንድ አካል የሆኑት የወላይታ ሶዶ፣ የሐረር፣ የሻሸመኔ፣ የደብረማርቆስ፣ የጎንደር እና የኮምቦልቻ ከተሞች 69.38 በመቶ አፈጻፀም ላይ እንደሚገኝና ቀሪ ስራዎችን በሚቀጥለው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል፡፡

በሎት አንድ እየተከናወነ የሚገኘው የወላይታ ሶዶ እና ሐረር ከተሞች የዲስትቡሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታ ስራ 61.1% ላይ የደረሰ ሲሆን 5 ሺህ 3 መቶ 95 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ መከናወኑን ታውቋል፡፡

በሎት ሁለት እየተከናወነ የሚገኘው የሻሸመኔ እና ደ/ማርቆስ ከተሞች የዲስትቡሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታ ስራ 79.47 % ላይ መድረሱንና እስካሁን 7 ሺህ 1 መቶ 32 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ መሰራቱን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡

በሎት ሶስት እየተከናወነ የሚገኘው የጎንደር እና ኮምቦልቻ ከተሞች የዲስትቡሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታ ስራ ደግሞ 50.6% የአፋጻፀም ደረጃ ላይ መድረሱንና እካሁን 2 ሺህ 2 መቶ 63 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ እንዲሁም የ12.49 ኪ.ሜ የዝቅተኛ ቮልቴጅ ኬብል ዝርጋታ ስራ መሰራቱን በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡

በአዴል (ADELE) ፕሮግራም ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር ለሚሰሩ የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራዎች አስፈላጊ የሆኑ የጨረታ ሰነድ ዝግጅትና የአማካሪ ድርጅቶች ቅጥርና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

በዚህ ፕሮግራም ተካተው እየተሰሩ የሚገኙት 4ኛ ዙር የአዲስ አበባ ዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት እና የ10 ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማለትም የቢሾፍቱ፣ የደብረብረሃን፣ የሱሉልታ፣ የአምቦ፣ የነቀምት፣ የአሶሳ፣ የሆሳእና፣ የዲላ፣ የአሰላ እና የጅጅጋ ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራ የኔትዎርክ መረጃ የማጥራትና ሎሎች ተያያዥ የዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በሃገሪቱ የተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች፣ ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ መናር፣ የኮንክሪት ምሰሶ አቅርቦት እጥረትና የመሳሰሉ ችግሮች እየተከናወኑ የሚገኙ የዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ የስራ ሂደት ላይ ያጋጠሙ አሉታዊ ተፅኖ ያሳደሩ ችገርች መሆናቸውን ተገልጿል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.8K views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:46:15
4.4K views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 09:16:50 ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
*************************
የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅረቦት ፕሮግራም ጽ/ቤት በ2014 በጀት አመት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን እውን ለማድረግ በሰራው ስራ 204 የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ይህ የተገለፀው ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ፒራሚድ ሆቴልና ሪዞርት ባካሄደው የ2014 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማና የ2015 በጀት አመት ዕቅድ ውይይት ላይ ነው፡፡

የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በበጀት አመቱ 2 መቶ 50 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ 68 ሺህ 3 መቶ 64 ደንበኞችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ከቀረቡው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡

ለደንበኞች ቆጣሪ በማገናኘት ለመሰብሰብ ካቀደው 253 ሚሊዮን 673 ሺህ 9 መቶ 95 ነጥብ ከ 85 ሳንቲም ውስጥ 73 ሚሊዮን 413 ሺህ 7 መቶ 75 ከ22 ሳንቲም መሰብሰብ ችሏል፡፡

ከመስመር ዝርጋታ አንጻር 4 ሺህ 2 መቶ 50 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ለመዘርጋት አቅዶ 2 ሺህ 4 መቶ 96.69 ኪ.ሜ በመዘርጋት የዕቅዱን 58 ነጥብ 75 በመቶ መፈፀም ችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 2 ሺህ 52 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ለመዘርጋት አቅዶ 1 ሺህ 9 መቶ 23.78 ኪ.ሜ በመዘርጋት የዕቅዱን 93 ነጥብ 75 በመቶ አፈጻጸም ያስመዘገበ ሲሆን 1 ሺህ 66 ትራንስፎርመሮች ለመትከል አቅዶ 5 መቶ 55 ትራንስፎርመሮችን በመትከል የዕቅዱን 52 በመቶ መፈፀም ችሏል፡፡

ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው የሚገኙ የገጠር መንደሮችንና ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ የሚገኘው የ12 የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሳይቶች ውስጥ 10ሩ ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንና ቀሪዎቹ በሂደት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር እየተከናወነ የሚገነው የ25 ከተሞች የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አካል የሆኑት የዳራቶሌ፣ የሂግሎሌ፣ ቦኮሎማዮ እና የእርጎየ ሳይቶች ላይ የግንባታ ስራ መጀመሩና በቀሪ ሳይቶች ላይ የዲዛይን፣ የውጭ እቃዎችን የማስገባት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ከዓለም ባንክ በተገኘ 400 ሚሊዮን ዶላር ከ200 በላይ የገጠር መንደሮችና ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ተግራዊ እየተደረገ የሚገኘው የአዴል (ADELE) ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር የዳሰሳ ጥናት ከተካሄደባቸው 114 መንደሮች ውስጥ 83 ከተሞች አዋጪ መሆናቸውን ተረጋግጧል፡፡

የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በአካባቢው የሚገኙ የጤና፣ የትምህርት፣ የውሃ ተቋማት፣ የእርሻ ማዕከላት፣ ወፍጮ ቤቶች እና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ የህብረረሰቡን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል ላይ እንደሚገኙ ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡

በመጨረሻም በሃገሪቱ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች፣ የኮንትራክተሮች የመፈፀም አቅም ውስንነት፣ ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የሲምንቶ ዋጋ ንረት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና መሰል ችግሮች የተጀመረውን ኤሌክትሪክ የማዳረስ ስራ በተፈለገው መጠን እንዳይከናወን እንቅፋት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተጣለበትን ኤሌክትሪክ የማዳረስ ሃገራዊ ሃላፊነት እውን ለማድረግ በብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም እ.ኤ.አ በ2025 ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጮች 35 በመቶ የሚሆነውን ህብረተሰብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑ ይታወቀል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et/
5.1K views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ