Get Mystery Box with random crypto!

በፕሮጀክቶች የአፈጻፀም ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቀነስ የሚያስችሉ የክትትልና የቁጥጥር ስ | Ethiopian Electric Utility

በፕሮጀክቶች የአፈጻፀም ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቀነስ የሚያስችሉ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ተገለፀ
*****************************
በፕሮጀክቶች የአፈጻፀም ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቀነስ የሚያስችሉ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ለምልም ምስጋናው ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሯ ይህን የገለፁት ከሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሶሰት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በቆየው የ2014 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማና የ2015 በጀት አመት ዕቅድ ውይይት ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡

በዕቅድ አፈጻፀም ግምገማው የማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት ወ/ሮ ለምለም ከፕሮጀክት አፈጻፀም ጋር የተያያዙ ችግሮች ለመፍታና የሚከናወኑፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ተገቢ የሆነ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ማከናወንና ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዳይሬክተሯ አክለውም በኦፍ ግሪድ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ መጓተቶች በተለይም ደግሞ በ12 አነስተኛ የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ላይ ያሉ ቀሪ ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚገባና ለፕሮጀክቶች መጓተት እንደ ምክንያት የሚቀርቡ የፀጥታ ችግሮች ትክክለኛ መሆንና አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

ከኮንክሪት የፖል አቅርቦት ጋር ተያይዞ ችግርሮችን ለመፍታት የአምራቾችን አቅም ባገነዘበ መልኩ ግዥ በመፈፀም ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የኮንሰንትሪክ ኬብል እጥረት ችግርን ለመፍታት በራሳቸው አቅም ማቅረብ ለሚችሉ ደንበኞች እድሉን እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ የገለፁት ዳይሬክተሯ በራሳቸው ማቅረብ ለማይችሉ ደንበኞች በተቋሙ በኩል ሊሠሩ የሚችሉ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ማስተናገድ እንደሚገባም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ከዋናው የኃይል ቋት እስከ 2.5 ኪሜ ርቀት ላይ ለሚገኙ ከተሞች የትራንስፎርመር እጥረት ከታየ የሶይል ትራንስፎርመር በአማራጭነት መጠቀም እንደሚያስፈልግም መመሪያ ተሰጥተዋል፡፡

ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በየደረጃው ከሚገኙ የክልልና የከተማ መስተዳደር አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የክልል ቢሮዎች ከሚያወጧቸው ወጪዎች ጋር የሚመጣጠን ስራ ሊያከናውኑ እንደሚገባና ከንብረት ብክነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመከላከልም ተገቢ የሆነ ክትትልና ቁጥር ሊደርጉ እደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ፒራሚድ ሆቴልና ሪዞርት ሲያካሂድ የቆየው የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት የ2014 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማና የ2015 በጀት አመት ዕቅድ ውይይት በበጀት አመቱ የታዪ ጠንካራና ደካማ ጎናችን በመለየትና በቀጣይ የተሻለ ስራ ለማከናወን የሚያስችሉ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et