Get Mystery Box with random crypto!

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኤሌክትሪክ አቅርቦት /በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች/ ***** | Ethiopian Electric Utility

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኤሌክትሪክ አቅርቦት /በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች/
********************
በሮቤ ሰብሰቴሽን ባጋጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በሮቤ፣ በአጋርፋ፣ በሲና ከተማና አካባቢያቸው በከፊል እንዲሁም ጋሰራ ከተማና አካባቢው ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

ወቅቱ ከባድ ዝናብ የሚጥልበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጥገና ስራው አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ችግሩ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ አፋጣኝ እልባት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በአካባቢዎቹ የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን፤ የጥገና ሥራው ተጠናቆ ችግሩ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et