2022-09-09 09:30:00
በአገር አቀፍና አለም አቀፍ ውድድሮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተወዳዳዎች ሽልማት ተበረከተላቸው
*************************
የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ትናንት ጷጉሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ባካሄደው የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም በአገር አቀፍና አለም አቀፍ ውድድሮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ሽልማት አበርክቷል፡፡
በእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚና የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የስፖርት ክለብ ጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ አሰፋ ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴረሽን ፕሬዘዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጫላ አማን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የእውቅና ሽልማቱ የተበረከተው በብስክሌት፣ በቴንስ, በታዳጊ ሴት የእግር ኳስ እና በአትሌቲክስ ውድድሮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተወዳደራዎች ነው፡፡
በእውቅና ሽልማቱ ስነ-ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚና የክለቡ ጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ተሊላ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የስፖርት ክለብ በሃገሪቱ የስፖርት ዘርፍ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት አድንቀው፤ በቀጣይም ከዚህ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴረሽን ፕሬዘዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ በበኩላቸው ሃገሪቱ ላስመዘገበቻቸው አለም አቀፍና አገር አቀፍ የውድድሮች ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስዱት የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የስፖርት ክለብ ተወዳዳሪዎች መሆናቸውን ገልፀው፤ ከዚህ የተሻለ ውጤቱ ለማስመዝገብ የተጀመረው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
በእውቅና ሽልማት ፕሮግራሙ ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ አባል ለሆነቸው እና በ18ኛው የኦሪገኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገበችው አትሌት ጎይትቶም ገብር ስላሴ 3 መቶ ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላታል፡፡
የክለቡ የወንዶች የእግር ኳስ ቡድን ወደ ፕሪሜርሊጉ ሲያድግ መሰል የእውቅናና ሽልማት መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.9K viewsedited 06:30