Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.33K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 42

2022-08-29 18:38:25 የተቋሙ መሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ዓመታዊ ጉባዔውን እያካሄደ ነው
********************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ምክር ቤት ዛሬ ነሀሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን አያካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የምክር ቤቱ ሊቀመንበር አቶ ሃይሉ ዘውዴ፣ ከሁሉም የክልልና የከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤቶች እና ዲስትሪክቶች የተወጣጡ የምክር ቤት አባላት ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

የጉባዔው ዋና ዓላማ ሰራተኛ ማህበሩ የ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የኦዲት ሪፖረት ማድመጥ የቀጣይ በጀት የትኩረት አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ነው፡፡

በክብር እንግድነት የተገኙት የተቋሙ ዋና ስራ አስፋጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ባስተላለፉት መልዕክት ለተቋሙ ህልውና የሰራተኛውን አቅም ማጎልበት ተገቢ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ተቋሙ ያስቀመጠውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት እንዲቻል የሰራተኛውን ጥቅም ማስጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ሃይሉ ዘውዴ በበኩላቸው በተጠናቀቀው በጀት አመት የሰራተኛውን መብትና ጥቅም ማስከበር፣ የሰራተኛውን ጤናና የስራ ላይ ደህነትን ማስጠበቅ፣ ከአቻ ማህበራት ጋር የልምድ ልውውጥና ስልጠናዎችን ማመቻቸት፣ ለአዳዲስ ሰራተኞች ቅደመ ስልጠና ማዘጋጀት እንዲሁም የሰራተኞችን ጥቅማ ጥቅምን ከማስከበር አንጻር አመርቂ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡

ሊቀመንበሩ አክለውም ከሰራተኞች የሚመጡ ቅሬታዎችን በደንብ በማጤን የተቋሙን ህግና ደንብ በተከተለ መልኩ ከሚመለከታቸው አካለት ጋር በመነጋጋገር ምላሽ እንዲሰጥባቸው መደረጉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የእድገትና ዝውውር ማስታወቅያዎችን አለማዳረስ፣ የጋራ ኮሚቴ ላይ የሚሳተፉ አመራሮች ግንዛቤ ማነስ፣ በየማዕከሉ የዘርፋ ማህበራት አለመኖር እና ም/ቤቱ ያፀቀውን ዕቅድ ሙሉ ለሙሉ አለመፈጸም በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንደነበሩ ጠቁመዋል፡፡

በዕለቱም የሰራተኛ ማህበሩ የሂሳብ ሹም የሆኑት ወ/ሮ ንብረት ዓላምራው የማህብሩን የገቢ እና ወጪ ሂሳብ እንደሁም መነሻ ካፒሉን የተመለከተ የኦዲት ረፖርቱን ለማህበሩ አባላት አሰምተዋል፡፡

በመጨረሻም የመሰረተዊ የሰራተኛ ማህበሩ የተጣለበትን ሃለፊነትና ተግባር አቅሙ በፈቀደ መጠን ለማሳካትና የሰራተኛውን መብትና ጥቅም ከመቸውም ጊዜ በላይ ለማስከበር በቅንጅት እንደሚሰራ አቶ ሀይሉ አስገንዝበዋል፡፡

ዛሬ የተጀመረው መሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ዓመታዊ ጉባዔ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ከተሰጠ በኋላ በነገው ዕለት የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
7.0K viewsedited  15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:38:20
4.5K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:18:01 በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ የሚፈፀም ስርቆትና የሚያስከትለው ተጠያቂነት
******************
በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ጉዳቶችና ስርቆቶች በተቋሙ አጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ እና በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያመጡት አሉታዊ ተፅዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

መሰል እኩይ ተግባር ለኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥና መዋዠቅ መንስኤ ሲሆን፤ በደንበኛውም ሆነ በተቋሙ እንዲሁም በሃገር ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያደርሳል፡፡

ባለፈው በጀት አመት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚያስተዳድራቸው የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ በተፈፀሙ ስርቆቶችና ባልተገባ የኃይል አጠቃቀም ምክንያት 130 ሚሊየን 984 ሺህ 279 ብር ኪሳራ ደርሷል፡፡

ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰቦችን ለህግ ተጠያቂ ለማድረግ በተሰራው ሥራም በ36 መዝገቦች ላይ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የመጨረሻ ውሳኔ በ64 ተከሳሾች ላይ ከ6 ወር እስከ 12 ዓመት ጽኑ እስራት ተወስኖባቸዋል፡፡

ሆኖም ይህ ዕኩይ ድርጊት ከህግ አስከባሪ አካላት፣ ከህብረተሰቡና ከተቋሙ ጋር በተቀናጀ መልኩ ካልተገታ በስተቀር አሁንም እየተባባሰ ይገኛል፡፡

በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ የሚፈፀም ስርቆትን ለመከላከልና ተፈጽሞ ሲገኝ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የኢነረጂ አዋጅ ያለ ሲሆን፤ በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ ስርቆት የሚፈጽም ወይም ጉዳት የሚያደርስ አካል በኢነርጅ አዋጅ 810/2006 አንቀጽ 26 እና 29 ተጠያቂ ይሆናል፡፡

በኢነርጅ አዋጅ 810/2006 አንቀጽ 26 መሰረት በማመንጫ፣ በማሰተላለፊያ ወይም በማከፋፈያ ተቋማት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 15 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ወይም እስከ ብር 50 ሺህ የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡

በኢነርጅ አዋጅ 810/2006 አንቀጽ 29 ደግሞ፡-

• ማንኛውም ሰው በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ማናቸውንም ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ነገር ያስቀመጠ ወይም የኤሌክትሪክ እቃ ያስቀመጠ፣ የተከለ ወይም የዘረጋ ወይም እንዲተከል፣ እንዲያገናኝ ወይም እንዲዘረጋ የፈቀደ፣

• በተከለለ የኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ይዞታ ውስጥ የገባ፣ ያረሰ፣ የቆፈረ፣ በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወይም የሚያውኩ ግንባታዎችን አላፈርስም፤ ዛፎችን አልቆርጥም ወይም አልመለምልም፣ ሰብሎችን፣ አትክልቶችን ወይም ሌሎች ነገሮችን አላስወግድም ያለ፣

• የተገጠመለትን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ያሰናከለ ወይም እንዲሰናከል የፈቀደ ወይም የኤሌክትሪክ ፍጆታን እንዳይመዘገብ ያደረገ ወይም የተባበረ፣

• የይሁንታ ማረጋገጫ ሳይኖረው በተዘረጋለት የኤሌክትሪክ መሰመር ላይ ማናቸውንም ለውጥ ያደረገ ወይም እንዲደረግበት የፈቀደ፣ በማናቸውም መንገድ የኤሌክትሪክ ኃይል ሊጠቀም ከተዋዋለበት ተግባር ውጭና ከተፈቀደለት ኤሌክትሪክ መጠቀሚያ እቃዎች ውጭ የተጠቀመ፣

• የተሰጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማንኛውም ሌላ ሰው አሳልፎ የሰጠ፤

• ማናቸውንም የኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ አካላትን ያለያየ፣ የሰረቀ ወይም በማለያየቱና በስርቆቱ የተባበረ፣

• በኤሌክትሪክ መሰመሮች ላይ ሆን ብሎ ወይም በግዴለሽነት ጉዳት በማድረስ ያቋረጠ፣

እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ወይም ከብር 25 ሺህ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ወይም ሁለቱንም እንዲቀጣ ይደነግጋል፡፡

በመሆኑም አውቀውም ይሁን ባለማወቅ ተባባሪ በመሆን በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት ወይም ጉዳት የሚያደርሱ አካላት ከእኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ህብረተሰቡም የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን እንደራሱ ንብረት መንከባከብና መጠበቅ እንዲሁም አጠራጣሪ ጉዳይ ሲመለከትም ለህግ አስከባሪ አካላት መጠቆም ይገባዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የሚነካኩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙ በተቋሙ የተመደቡ ሠራተኞች መሆናቸውን የሚገልፅ መታወቂያ መያዛቸውን በመጠየቅ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግና በአከባቢው በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድ ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የሁላችንም ሃብት ነው፡፡ በጋራ እንጠብቀው!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
6.2K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:14:28
5.1K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:22:26
ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ በቴሌብር #መተግበሪያ ለመክፈል የሚከተሉትን ቅድመ ተከተሎችን ይጠቀሙ!
5.3K views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:49:38 ለፍጆታ የተሰጠን የኤሌክትሪክ ኃይል ያላግባብ መጠቀም ጉዳቱና ተጠያቂነት
************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ጥራት ያለው ለማድረግ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተደገፈ የክፍያ ስርዓት ተግባራዊ ከማድረጉ ጎን ለጎን ተከታታይነት ያላቸው የሱፐርቪዥንና የቆጣሪ ምርመራ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

መሰል ስራ መሰራቱ የኃይል ብክነቶችን ለመቀነሰ እንዲሁም ለፍጆታ የተሰጠን የኤሌክትሪክ ኃይል ያላግባብ በሚጠቀሙ ደንበኞች ላይ ተገቢ የሆኑ ማስተካከያዎችን ለማድረግም ያስችላል፡፡

ያላግባብ የሆነ አጠቃቀም ደግሞ ለደንበኞች የሚቀረበውን የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥና እንዲዋዥቅ የሚያደርግ ሲሆን፤ በደንበኛውም ሆነ በተቋሙ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡

በተጨማሪም ደንበኛውን ለቅጣት፣ ለወጪና ለተጠያቂነት እንዲሁም ተቋሙንም ለኪሳራ የሚዳርግ ተግባር ነው፡፡

ይህ ድርጊት ከሚያስከትለው ጉዳት ጎን ለጎን በተጠቃሚው ላይ የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ተጠያቂነትም ያስከትላል፡፡

በመሆኑም ማንኛው ደንበኛ ለፍጆታ የተሰጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል በአግባቡ መጠቀምና ያላግባብ የሆነ አጠቃቀምንም ከመከላከል አንፃር የራሱን ሚና መወጣት ይኖርበታል፡፡

ከዚህም አንዱ በቅድሚያ ከተቋሙ ጋር ውል ፈፅሞ ኤሌክትሪክ እንዲጠቀም ቆጣሪ የተፈቀደለት ማንኛውም ደንበኛ ተገቢ የሆነ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ መሰል ድርጊት ሊከላከል ይገባል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ያለው ቤት ግዥ የሚፈፅም ግለሰብ ቤቱን ከመረከቡ በፊት በአቅራቢያ በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመቅረብ ውዝፍ የፍጆታ ዕዳዎችን ማጣራት፣ ቆጣሪው ከወንጀል ድርጊት የፀዳ መሆኑን ማረጋገጥ እና ከተቋሙ ጋር ውል እንደገና ማደስ ይጠበቅበታል፡፡

ህግን ከማስከበር አኳያ እንዲሁም በደንበኞች የሚፈፀሙ ያላግባቡ የኃይል አጠቃቀም ለመከላከል እና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እንደ ሃገር የኢነርጂ አዋጅ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ ውሏል፡፡

በኢነርጂ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 810/2006 መሰረት ማንኛውም ግለሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል የሰረቀ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ከሌላ ጋር ያገናኘ፣ መስመር ያሰናከለ ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል ኢንዲሰረቅ ከሌላ መስመር ጋር እንዲገናኝ ወይም መስመሩ እንዲሰናከል ያደረገ ወይም መስመሩ የተሰረቀ፣ በሕገወጥ መንገድ ከሌላ መስመር ጋር የተገናኘ ወይም የተሰናከለ መሆኑ እያወቀ ከዚሁ መስመር ማናቸውም የኤሌክትሪክ ኃይል ለፍጆታ ያዋለ ወይም የተገለገለ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ከተፈቀደለት የኃይል አጠቃቀም ውጭ ሲጠቀም የተገኘ ማንኛውም ደንበኛ በሃገሪቱ የኢነርጂ አዋጅ መሰረት በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን ይህ አዋጁ በግልፅ ይደነግጋል፡፡

አዋጁን ተላልፎ ያላግባብ የኤሌክትሪክ ኃይል ሲጠቀም የተገኘ ማንኛውም አካል በሕግ ከመጠየቁም በተጨማሪ ይጠቀምበት የነበረው ቆጣሪ እንደሚቋረጥበት እና ያላግባብ ለተጠቀመው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በታሪፉ መሰረት ተሰልቶ ከዳግም ማስቀጠያ ክፍያ እና ከቅጣት ገንዘብ ጋር እንዲከፈል ይደረጋል፡፡

ስለሆነም ከመሰል ቅጣትና ተጠያቂነት ለመዳን እንዲሁም የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል ማንኛውም ደንበኛ የሚገለገልበትን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ከተቋሙ ጋር በገባው ውል መሰረት ብቻ እንዲጠቀምና ቤት አካራዮችም በየጊዜው አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርጉ ተቋሙ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

በመጨረሻም ከቆጣሪ ጋር የተገናኘ ማንኛውም አይነት ችግር ካጋጠመ በአካባቢ ወደ ሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመቅረብ ወይም በ905 ነፃ የጥሪ ስልክ በመደወል ጥቆማ መስጠት ይቻላል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
13.0K views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:49:31
7.8K views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 14:29:04 ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት በቀላሉ ማወቅ ይቻላል?
*************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአሁን ወቅት ከ3 ነጥብ 32 ሚሊዮን በላይ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች አሉት፡፡ ከእነዚህ ደንበኞቹ መካከል በርካቶቹ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት እንደሚሰላ ባለማወቃቸው የተጋነነ የፍጆታ ሂሳብ የተጠየቁ እየመሰላቸው ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ይስተዋላል፡፡

ይሁን እንጂ ቅሬታው የሚነሳው ደንበኞች የተጋነነ ሂሳብ እንዲከፍሉ በመደረጉ ሳይሆን የኤሌክትሪክ ኃይልን በአግባቡና በቁጠባ ባለመጠቀም እንዲሁም የፍጆታ ሂሳብ እንዴት መሰላት እንዳለበት በቂ መረጃ ካለመያዝ የመነጨ ነው፡፡

ስለሆነም የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች በመኖሪያ ቤታቸው የሚጠቀሙባቸውን የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች የኃይል መጠን መነሻ በማድረግ ምንያህል ኪ.ዋ.ሰ እንደተጠቀሙና ምን ያህል ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ እንደሚከፍሉ መረዳት ይችላሉ፡፡

ይህንንም በቀላሉ ለመረዳት እንዲያስችል የአንድ የመኖሪያ ቤት ድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛ የሆነ ሰው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ስሌቱ በሚቀጠለው ምሳሌ እናስቀምጠው፡-

• አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤቱ 4 ባለ 60 ዋት አምፖሎች በቀን ለ6 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢያበራ፣

• 3000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ በቀን ለ2 ሰዓት በወር ለ10 ቀናት ቢጠቀም፣

• 1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ በቀን ለ5 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢጠቀም፣

እና ይህ ግለሰብ ሌሎች የኤሌክትሪክ መገልገያ ቁሳቁሶች ሳይጨምር በወር ውስጥ ምን ያህል ኪ.ዋ.ሰ እንደተጠቀመና ምን ያህል የፍጆታ ሂሳብ እንደሚከፍል ለማወቅ የተጠቀመበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በመደመር ወደ ኪ.ዋ.ሰ መቀየር ይጠበቅበታል፡፡

በዚህም መሰረት
 4 አምፑል X 60 ዋት x 6 ሰዓት x 30 ቀናት = 43,200 ዋት.ሰ፣
 3000 ዋት ኤሌክትሪክ የኃይል የሚጠቀም ምጣድ x 2 ሰዓት x 10 ቀናት = 60,000 ዋት.ሰ፣

 1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ x 5 ሰዓት x ለ30 ቀናት = 150,000 ዋት.ሰ፣

ሶስቱም ሲጠቃለሉ 43,200 ዋት.ሰ + 60,000 ዋት.ሰ + 150,000 ዋት.ሰ = 253,200 ዋት.ሰ ይሆናል፡፡ ይህም ወደ ኪሎ ዋት ሰዓት መቀየር አለበት፡፡
1 ኪሎ ዋት ሰዓት = 1000 ዋት ሰዓት በመሆኑ፤ 253,200 ዋት ሰዓት = 253.2 ኪሎ ዋት ሰዓት ይሆናል፡፡

የመኖሪያ ቤት የታሪፍ ስሌት 7 ደረጃዎች ያሉት ሲሆን፤ አንድ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ በወር የተጠቀመበት የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያርፍበት የታሪፍ እርክን ተባዝቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

በዚህ ስሌት መሰረት ከላይ በምሳሌው የጠቀስነው ደንበኛ በወር 253.2 ኪ.ዋ.ሰ የኤሌክትሪክ ኃይል የተጠቀመ በመሆኑ በቀጥታ 4ኛው እርከን ላይ ያርፋል፤ በመሆኑም በ2.0000 ብር ይባዛል፡፡

በዚህ መሰረት 253.2 ኪ.ዋ.ሰ x 2.0000 ብር= 506.4 ብር ይመጣል፡፡
የአገልግሎት ክፍያ ብር 42 ሲደመርበት በአጠቃላይ ይህ ደንበኛ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳቡ 548 ብር ከ 4 ሳንቲም ይሆናል ማለት ነው፡፡

ስለሆነም ደንበኞች የምትጠቀሙባቸው የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች የሚጠቀሙትን የኃይል መጠናቸው በመለየትና በቀን ውስጥ የምትገለገሉበት ጊዜ በማወቅ ወርሃዊ ፍጆታችሁን በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁ፡፡

ገንዘባችሁ ይበልጥ ለመቆጠብ ደግሞ በቤት ውስጥ ኃይል ቆጣቢ የኤሌክትሪክ መገልገያ ቁሳቁሶቹ መጠቀም፤ የአጠቃቀም ሰዓት መለየትና የኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ማንኛውንም የቤት ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ሲገዙ የኃይል ቆጣቢ መሆናቸዉን ማረጋገጥ፣ ረዥም ጊዜ ያገለገሉ የቤት ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በአዲስ መቀየር፣ ሁሉንም የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አገልግሎት በማይሰጡበት ጊዜ ማጥፋትና ሶኬቶችንም መንቀል ተገቢ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
10.0K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 14:28:57
6.8K views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 11:45:14
የኢኤአ የሳምንቱ አበይት መረጃዎች ሲታወሱ
**************
• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተልዕኮውን ለማሳካት ከለያቸው የትኩረት መስኮች አንዱ የሆነውን ሥራዎችን በሶሰተኛ ወገን ማሰራት በሚመለከት ከፅዳትና ጥበቃ አገልግሎት ሠራተኞች ጋር ግልፅነትን ለመፍጠር ያለመ የምክክር መድረክ ማካሄዱን፣

• የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ በ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና በ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም በአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ መስጠታቸውን፣

• የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በጥንቃቄ ጉድለት በሚያከናውነው የመንገድ ግንባታ 10 ሚሊየን 607 ሺህ 391 ብር የሚገመት ከመሬት በታች በተቀበረ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት መድረሱን የደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ማስታውቁን፡፡

• የ6ቱ ከተሞች የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት አካል የሆነው የደብረ ማርቆስ ከተማ የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ ከ85 ፐርሰንት በላይ መድረሱን ዋና ዋና አበይት መረጃዎቻችን ነበሩ::

ሠናይ ቅዳሜና ዕሁድ እንዲሆንላችሁ ተመኘን!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
7.7K viewsedited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ